ግንቦት 24, 2022
ሩሲያ
የሶቺ የይሖዋ ምሥክሮች ቢፈረድባቸውም በእምነታቸው ጸንተዋል
መጋቢት 28, 2022 በሶቺ የሚገኘው የኮስቲንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት የወንድም ቭላድሚር ዴሽኮን፣ ዩሪ ሎጂንስኪን፣ ዩሪ ሞስካሌቭን እና የእህት ታትያና ቬሊዣኒናን ክስ ተመልክቶ ብይን አስተላልፏል። ወንድም ዴሽኮ አንድ ዓመት ከአራት ወር፣ እህት ቬሊዣኒና ደግሞ አንድ ዓመት ከአምስት ወር እስራት ተፈርዶባቸዋል። ሁለቱም የተፈረደባቸውን ጊዜ ያህል ማረፊያ ቤት ስለቆዩ እስር ቤት አይገቡም። ወንድም ሎጂንስኪ እና ሞስካሌቭ ደግሞ የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። እነሱም ቢሆኑ እስር ቤት አይገቡም።
የክሱ ሂደት
መጋቢት 24, 2021
አራቱም ተይዘው ጣቢያ ተወሰዱ፤ ለጊዜው እዚያ እንዲቆዩ ተደረገ። በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴዎች ተሳትፈዋል ተብለው ተከሰሱ
መጋቢት 26, 2021
ወንድም ዴሽኮ እና እህት ቬሊዣኒና 400 ኪሎ ሜትር ርቆ ወደሚገኝ ማረፊያ ቤት ተላኩ። ወንድም ሎጂንስኪ እና ሞስካሌቭ የቁም እስረኛ ተደረጉ
የካቲት 3, 2022
ወንድም ዴሽኮ ከማረፊያ ቤት ተለቅቆ የቁም እስረኛ ተደረገ
መጋቢት 3, 2022
ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
መጋቢት 4, 2022
እህት ቬሊዣኒና ከማረፊያ ቤት ተለቅቃ የቁም እስረኛ ተደረገች
አጭር መግለጫ
በእነዚህ አስቸጋሪ የመጨረሻ ቀናት ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹን እንደሚደግፍ፣ እንደሚያበረታና ለመጽናት የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ እንደሚያደርግላቸው እንተማመናለን።—መዝሙር 89:21