በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ኢልዳር ኡራዝባኽቲን

ጥቅምት 18, 2022
ሩሲያ

“የይሖዋን ስም በመሸከሜ እኮራለሁ!”

“የይሖዋን ስም በመሸከሜ እኮራለሁ!”

ጥቅምት 10, 2022 በክራስናያርስክ ክልል የሚገኘው የኬዤምስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ኢልዳር ኡራዝባኽቲን ላይ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል። የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶበታል፤ አሁን ወህኒ አይወርድም።

የክሱ ሂደት

  1. ሐምሌ 20, 2021

    በኮዲንስክ ከተማ ውስጥ ቢያንስ የአምስት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ተበረበሩ፤ አንደኛው ቤት የኢልዳርና የቤተሰቡ መኖሪያ ነው። ኢልዳር ወደ ጣቢያ ተወሰደ

  2. ሐምሌ 21, 2021

    ከጣቢያ ተለቅቆ የቁም እስረኛ ተደረገ። ስልክም ሆነ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ታገደ

  3. መስከረም 20, 2021

    ከቁም እስር ተፈታና የጉዞ እገዳ ተጣለበት

  4. ጥር 13, 2022

    የቪዲዮ ኮንፈረንስ በማድረግ “ወንድሞችና እህቶች መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት እንዲያጠኑና እርስ በርስ እንዲደጋገፉ አበረታቷል” ተብሎ ተከሰሰ

  5. መጋቢት 30, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

የኢልዳርም ሆነ የሌሎቹ የሩሲያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ተሞክሮ እንደሚያጎላው አምላካችን ይሖዋ “በጭንቅ ጊዜ” የሚደርስልን አምላክ ነው።—መዝሙር 46:1