በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ቭላዲሚር ባላብኪን (መሃል) ከእስር ከተለቀቀ በኋላ ከባለቤቱ ከታትያና እና ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር ከፍርድ ቤቱ ውጭ ቆመው

ታኅሣሥ 25, 2023
ሩሲያ

የ71 ዓመቱ ወንድም ቭላዲሚር ባላብኪን ከእስር ተለቀቀ

የ71 ዓመቱ ወንድም ቭላዲሚር ባላብኪን ከእስር ተለቀቀ

ታኅሣሥ 19, 2023 ወንድም ቭላዲሚር ባላብኪን ከተበየነበት የአራት ዓመት እስራት ውስጥ ከሦስት ወር ብዙም ያልበለጠ ጊዜ ብቻ ከቆየ በኋላ ከእስር ተለቀቀ። ጥፋተኛ ነው ተብሎ የተፈረደበት መስከረም 13, 2023 ነበር። ቭላዲሚር የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ይግባኝ ጠየቀ። ይግባኙን የተመለከቱት ሦስት ዳኞች የመጀመሪያው ብይን እንዲቀየር ወሰኑ። በመሆኑም ቅጣቱ ከአራት ዓመት እስራት ወደ አንድ ዓመት የገደብ እስራት ተቀየረ።

ክሱ በፍርድ ቤት በታየበት ወቅት ቭላዲሚር እንዲህ ሲል በድፍረት ተናግሯል፦ “የማምንባቸው ነገሮች የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ፈጣሪያችን በሁሉም ሰዎች ላይ ማየት የሚፈልጋቸውን እንደ ገርነት፣ ደግነት፣ ትዕግሥትና ራስን መግዛት ያሉ ባሕርያት እንዳዳብር ረድቶኛል። ይህም ራሴንም ሆነ ቤተሰቤን ጠቅሟል። ሁሉም ሰው የአምላክን ቃል ቢያውቀው ደስ ይለኛል፤ ምክንያቱም ቃሉ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል።”

ከወንድም ቭላዲሚርና ከቤተሰቡ ጋር አብረን እንደሰታለን፤ በተጨማሪም ይሖዋ ለጽናታቸው ወሮታ እንደሚከፍላቸው በመተማመን አሁንም በእስር ላይ ላሉት መጸለያችንን እንቀጥላለን።—ዕብራውያን 10:34