በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ዬቭጌኒ ዚኒች

ሐምሌ 7, 2022
ሩሲያ

ዬቭጌኒ ዚኒች የቤተሰቡን የታማኝነት ጎዳና ተከትሏል

ዬቭጌኒ ዚኒች የቤተሰቡን የታማኝነት ጎዳና ተከትሏል

ሰኔ 27, 2022 በክራስኖያርስክ የሚገኘው የኦክትያቢርስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት በወንድም ዬቭጌኒ ዚኒች ላይ የስድስት ዓመት እስራት በይኗል። ዬቭጌኒ ወዲያውኑ ከፍርድ ቤት ወደ እስር ቤት ተወስዷል።

የክሱ ሂደት

  1. ታኅሣሥ 11, 2020

    የዬቭጌኒ ቤት ተፈተሸ

  2. ጥር 21, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  3. ጥቅምት 19, 2021

    የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴዎች አስተባብሯል በሚል ክስ ተመሠረተበት

  4. ጥቅምት 20, 2021

    የጉዞ ክልከላዎች ተጣሉበት

  5. ታኅሣሥ 14, 2021

    ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ዬቭጌኒ ከባድ ፈተናዎችን ተጋፍጦ የቤተሰቡን የድፍረትና የጽናት ምሳሌ ለመከተል ጥረት ሲያደርግ ይሖዋ ፍቅሩን እንደሚያሳየውና እንደሚያጽናናው እንተማመናለን።—መዝሙር 86:17