በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ አሌክሳንደር ሶብያኒን፣ ቭላዲሚር ቲሞሽኪን እና ቭላዲሚር ፖልቶራድኔቭ

መስከረም 12, 2023
ሩሲያ

“ይሖዋ ሁልጊዜም ረዳታችን ነው!”

“ይሖዋ ሁልጊዜም ረዳታችን ነው!”

ነሐሴ 18, 2023 በፐርም ክልል የሚገኘው የሶሊካምስክ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም ቭላዲሚር ፖልቶራድኔቭ 638,000 ሩብል (6,787 የአሜሪካ ዶላር)፣ ወንድም አሌክሳንደር ሶብያኒን 494,000 ሩብል (5,255 የአሜሪካ ዶላር) እንዲሁም ወንድም ቭላዲሚር ቲሞሽኪን 512,000 ሩብል (5,447 የአሜሪካ ዶላር) ቅጣት እንዲከፍሉ ፍርድ አስተላለፈ። ፍርድ ቤቱ ጥፋተኞች ናቸው የሚል ብያኔ ያስተላለፈ ቢሆንም አሁን ወደ ወህኒ አይወርዱም።

አጭር መግለጫ

እምነታቸውን በይሖዋ ላይ የጣሉ ሁሉ በረከቱና ታማኝ ፍቅሩ እንደማይለያቸው እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 13:5, 6

የክሱ ሂደት

  1.  ሐምሌ 28, 2020

    ቤቶቻቸው ተፈተሹ። ሦስቱም ወንድሞች በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ተደረገ

  2.  ሐምሌ 29, 2020

    ቭላዲሚር ቲሞሽኪን ከማረፊያ ቤት ወጥቶ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ

  3.  ሐምሌ 30, 2020

    አሌክሳንደር ከማረፊያ ቤት ወጥቶ በጉዞ ገደብ ሥር እንዲቆይ ተደረገ

  4.  ሐምሌ 31, 2020

    ቭላዲሚር ፖልቶራድኔቭ ከማረፊያ ቤት ወጥቶ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ

  5.  መስከረም 24, 2020

    ቭላዲሚር ፖልቶራድኔቭ ከቁም እስሩ ነፃ ተለቆ የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  6.  ጥቅምት 26, 2020

    ቭላዲሚር ቲሞሽኪን ከቁም እስሩ ነፃ ተለቆ የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  7.  ግንቦት 16, 2023

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

a ወንድም ቭላዲሚር ቲሞሽኪን የሰጠውን አስተያየት ማግኘት አልተቻለም