በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አሌክሴ ፓሲንኮቭ

ግንቦት 23, 2024
ሩሲያ

‘ይሖዋ ከእኔ አይለይም’

‘ይሖዋ ከእኔ አይለይም’

በካራቻዬቮ ቺርኬሲያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የኡሩፕስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ከወንድም አሌክሴ ፓሲንኮቭ ክስ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍበት የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።

አጭር መግለጫ

የተለያየ መከራ ቢደርስብንም እንኳ ይሖዋ መጠጊያ እንደሚሆነን እና በእሱ ሐሴት ማድረግ እንደምንችል በማወቃችን አመስጋኞች ነን።​—መዝሙር 5:11

የክሱ ሂደት

  1. ኅዳር 23, 2021

    ባለሥልጣናቱ አሌክሴን በሥራ ቦታው ሳለ በቁጥጥር ሥር አዋሉት፤ ቤቱንም ፈተሹ

  2. ታኅሣሥ 8, 2022

    የክስ ፋይል ተከፈተበት

  3. መጋቢት 3, 2023

    ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ ተፈተሸ። አሌክሴ እና ዩሊያ ምርመራ ተደረገባቸው

  4. መጋቢት 31, 2023

    የአሌክሴ እናት እና ወንድሞች ቤት ተፈተሸ

  5. ጥቅምት 4, 2023

    የጉዞ እገዳዎች ተጣሉበት

  6. ታኅሣሥ 14, 2023

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ