በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አሌክሳንደር ካሊስትራቶቭ

የካቲት 20, 2023
ሩሲያ

“ይሖዋ ከእኔ ጋር እስካለ ድረስ የትም ቢሆን ቤቴ ያለሁ ያህል ይሰማኛል”

“ይሖዋ ከእኔ ጋር እስካለ ድረስ የትም ቢሆን ቤቴ ያለሁ ያህል ይሰማኛል”

በአልታይ ሪፑብሊክ የሚገኘው የጎርኖ አልታይስኪ ከተማ ፍርድ ቤት የካቲት 17, 2023 በወንድም አሌክሳንደር ካሊስትራቶቭ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል፤ በስድስት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት እንዲቀጣም ወስኗል። እርግጥ፣ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ፣ በጭንቅ ውስጥ ሆነው ለሚጠሩት ታማኝ አገልጋዮቹ አለኝታ መሆኑን እንደሚቀጥል እንተማመናለን።—2 ሳሙኤል 22:7

የክሱ ሂደት

  1. 2000

    ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ በቁጥጥር ሥር ዋለ። ለ21 ቀናት ማረፊያ ቤት ተላከ። በኋላ ላይ ከክስ ነፃ ተደረገ

  2. 2010

    በጽንፈኝነት ተከሰሰ። ክሱ በሁለት ፍርድ ቤቶች ከታየ በኋላ በአልታይ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፊት ቀረበ፤ በመጨረሻም ከክስ ሙሉ በሙሉ ነፃ ተደረገ

  3. ታኅሣሥ 16, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  4. ጥር 16, 2022

    ባለሥልጣናት በአልታይ ሪፑብሊክ የሚገኙ አምስት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶችን ፈተሹ። የፌዴራል ደህንነት አባላት የእነ አሌክሳንደርን ቤት ሰብረው ከገቡ በኋላ ለምርመራ እንፈልግሃለን ብለው ወሰዱት። በዚያው ምሽት ለቀቁት፤ ሆኖም የጉዞ ክልከላዎች ተጣሉበት

  5. ነሐሴ 25, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ