በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አናቶሊ ኢሳኮቭ እና ባለቤቱ ታቲያና

ጥር 1, 2024
ሩሲያ

‘ይሖዋ ፈጽሞ አልተወኝም’

‘ይሖዋ ፈጽሞ አልተወኝም’

በኩርጋን ክልል የሚገኘው የኩርጋን ከተማ ፍርድ ቤት በወንድም አናቶሊ ኢሳኮቭ ላይ ከተመሠረተው ክስ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍበት የሚፈልገውን ፍርድ ገና አላሳወቀም።

አጭር መግለጫ

አናቶሊ ብዙ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ቢኖሩበትም በቆራጥነትና በታማኝነት ረገድ የተወውን ምሳሌ እናደንቃለን። ደግሞም ምንም ዓይነት ፈተና ቢያጋጥመን ይሖዋ ‘የልባችን ዓለት’ እንደሚሆን ማወቃችን ያስደስተናል።​—መዝሙር 73:26

የክሱ ሂደት

  1. ሐምሌ 13, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተ

  2. ሐምሌ 14, 2021

    ቤቱ ተፈተሸ። ወደ ጊዜያዊ ማረፊያ ጣቢያ እንዲገባ ተደረገ

  3. ሐምሌ 15, 2021

    ወደ ማረፊያ ቤት እንዲዛወር ተደረገ

  4. ሐምሌ 21, 2021

    አናቶሊ ከማረፊያ ቤት ወጥቶ የኬሞቴራፒ ሕክምናውን እንዲቀጥል ለኩርጋን ክልል የጤና ክፍል ጥያቄ ቀረበ

  5. ነሐሴ 28, 2021

    የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ። ሆኖም የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  6. ሐምሌ 6, 2023

    ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ