በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ግንቦት 23, 2019
ሩሲያ

ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በዴኒስ ክሪስተንሰን ላይ የተላለፈው የእስራት ፍርድ እንዲጸና ወሰነ

ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በዴኒስ ክሪስተንሰን ላይ የተላለፈው የእስራት ፍርድ እንዲጸና ወሰነ

ሦስት ዳኞችን ያቀፈው የኦርዮል የክልል ፍርድ ቤት ግንቦት 23, 2019 በዋለው ችሎት፣ ዴኒስ ክሪስተንሰን ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ በማድረግ ቀደም ሲል የተበየነበት የስድስት ዓመት እስራት እንዲጸና ወስኗል። ወደ 80 የሚጠጉ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በፍርዱ ሂደት ላይ ተገኝተው ነበር። ከአውስትራሊያ እና ከዴንማርክ የመጡ ባለሥልጣናትም በቦታው ተገኝተው ነበር። ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈውን ውሳኔ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን እየዘገቡት ነው።

በየካቲት ወር በወንድም ክሪስተንሰን ላይ ፍርድ ከተላለፈ ወዲህ ባሉት ሦስት ወራት ውስጥ ባለሥልጣናቱ በይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ላይ 115 ጊዜ ፍተሻ አካሂደዋል፤ እንዲሁም በይሖዋ ምሥክሮች ላይ የተመሠረቱት ክሶች ከዚያ ቀደም በነበሩት ሦስት ወራት ከተመሠረቱት ክሶች ጋር ሲነጻጸሩ በሦስት እጥፍ ይበልጣሉ።

ለወንድም ክሪስተንሰንም ሆነ በሩሲያ ለሚገኙ የእምነት ባልንጀሮቻችን በሙሉ መጸለያችንን እንቀጥላለን። ይሖዋ “ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ” እንደሆነና ወንድሞቻችን የሚደርስባቸውን ስደት በጽናት እንዲቋቋሙ መርዳቱን እንደሚቀጥል እንተማመናለን—መዝሙር 145:18