ሐምሌ 12, 2023
ሩሲያ
ዲሚትሪ ቴሬቢሎቭ አብሮት ከታሰረ ሰው ጋር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ውይይት በማድረጉ በሩሲያ የወንጀል ክስ ተመሠረተበት
ሚያዝያ 20, 2023 የሩሲያ ባለሥልጣናት በወንድም ዲሚትሪ ቴሬቢሎቭ ላይ አዲስ ክስ መሥርተዋል፤ ዲሚትሪ ከመስከረም 2021 ጀምሮ በእምነቱ ምክንያት እስር ቤት ነው። በ2017 ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በይሖዋ ምሥክሮች ላይ እገዳ ከጣለ ወዲህ አንድ የይሖዋ ምሥክር አብሮት ከታሰረ ሰው ጋር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ውይይት በማድረጉ ምክንያት ክስ ሲመሠረትበት ይህ የመጀመሪያው ነው። ዲሚትሪ አዲስ በተመሠረተበት ክስ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እስከ ስምንት ዓመት የሚደርስ እስራት ሊፈረድበት ይችላል፤ ይህም በአሁን ወቅት ከታሰረበት የሦስት ዓመት ፍርድ በተጨማሪ ነው።
በሩሲያ በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የሚደርሰው ስደት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ቢሆንም ይሖዋ ለእነዚህ አገልጋዮቹ “ከሰብዓዊ ኃይል በላይ [የሆነውን] ኃይል” መስጠቱን እንደሚቀጥል ጠንካራ እምነት አለን።—2 ቆሮንቶስ 4:7