በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሦስት ዳኞችን ያቀፈው የኦርዮል የክልል ፍርድ ቤት በዴኒስ ክሪስተንሰን ላይ የተላለፈው የስድስት ዓመት እስራት ፍርድ እንዲጸና መወሰኑን ሲያስታውቅ

ሰኔ 11, 2019
ሩሲያ

ዴኒስ ክሪስተንሰን ለአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ይግባኝ ሊል ነው

ዴኒስ ክሪስተንሰን ለአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ይግባኝ ሊል ነው

ከዚህ በፊት እንደተገለጸው ግንቦት 23, 2019 የኦርዮል የክልል ፍርድ ቤት፣ በዴኒስ ክሪስተንሰን ላይ የተላለፈው ፍርድ እንዲጸና ወስኗል። በመሆኑም ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን ስድስት ዓመት ይታሰራል ማለት ነው። ወንድም ዴኒስ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከማሳለፉ በፊት ሁለት ዓመት ያህል ታስሮ ቆይቷል፤ በሩሲያ ሕግ መሠረት ደግሞ አንድ ሰው ያለ ፍርድ ይህን ያህል ጊዜ ከታሰረ ሦስት ዓመት እንደታሰረ ተደርጎ ይቆጠራል። ስለዚህ ወንድም ዴኒስ ፍርዱን ለመጨረስ ሦስት ዓመት ይቀረዋል ማለት ነው። በመሆኑም ሰኔ 6, 2019 ምሽት ላይ፣ እስረኞች የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ ወደሚገደዱበት ካምፕ እንዲዛወር ተደርጓል። ወንድም ዴኒስ የተላለፈበትን ውሳኔ በመቃወም ለአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ይግባኝ ሊል ነው። ከዚህ በፊት ያለ ፍርድ መታሰሩን አስመልክቶ ለአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ያቀረበው አቤቱታ በእንጥልጥል ላይ ነው።

ወንድም ዴኒስ እንዲህ ያለ ኢፍትሐዊ ድርጊት እየተፈጸመበት ቢሆንም ሳይረበሽ ሁኔታውን በጽናት መቋቋሙ የሚያስደንቅ ነው። ይሖዋ እሱንም ሆነ የወንጀል ክስ የተጋረጠባቸውን ከ200 የሚበልጡ በሩሲያ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች እንደሚረዳቸው እንተማመናለን።—መዝሙር 27:1

ዴኒስ ክሪስተንሰን ለኦርዮል የክልል ፍርድ ቤት ግንቦት 16, 2019 ያቀረበውን የመከላከያ መልስ አንብብ። (በአማርኛ አይገኝም)

ዴኒስ ክሪስተንሰን ለኦርዮል የክልል ፍርድ ቤት ግንቦት 23, 2019 ያቀረበውን የመከላከያ መልስ አንብብ። (በአማርኛ አይገኝም)