በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከላይ ከግራ ወደ ቀኝ፦ ኒና አስትቫትስቱሮቫ፣ ኤሌና ባርማኪ እና ልዩድቪጋ ካታናዬቫ

ከታች ከግራ ወደ ቀኝ፦ ኢጎር ሎንቻኮቭ፣ ዩሪ ርዬዶዙቦቭ፣ ዬካትዬሪና ትርዬጉባ እና ዬልዬና ትሶርን

ሐምሌ 25, 2023
ሩሲያ

ጸሎትና አዎንታዊ አመለካከት በቭላዲቮስቶክ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች እንዲጸኑ ረድቷቸዋል

ጸሎትና አዎንታዊ አመለካከት በቭላዲቮስቶክ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች እንዲጸኑ ረድቷቸዋል

በቭላዲቮስቶክ የፕዬርቮርዬችዬንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ከእህት ኒና አስትቫትስቱሮቫ፣ ከእህት ኤሌና ባርማኪና፣ ከእህት ልዩድቪጋ ካታናዬቫ፣ ከእህት ዬካትዬሪና ትርዬጉባ እና ከእህት ዬልዬና ትሶርን እንዲሁም ከወንድም ኢጎር ሎንቻኮቭ እና ከወንድም ዩሪ ርዬዶዙቦቭ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ፍርድ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍባቸው የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ጻድቅ አገልጋዮቹን ምንጊዜም እንደሚባርካቸውና እንደሚንከባከባቸው ማወቃችን በጣም ያጽናናናል፤ “[ሞገሱ] እንደ ትልቅ ጋሻ ይሆንላቸዋል።”—መዝሙር 5:12

የክሱ ሂደት

  1. ነሐሴ 6, 2019

    ኤሌና ባርማኪና የወንጀል ክስ ተመሠረተባት

  2. ሰኔ 8, 2020

    ኒና፣ ልዩድቪጋ እና ዬልዬና የክስ ፋይል ተከፈተባቸው

  3. ሰኔ 17, 2020

    የኤሌና ባርማኪና ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  4. ሐምሌ 9, 2020

    የኒና፣ የልዩድቪጋ፣ የዬልዬና እና የዩሪ ቤት ተፈተሸ። ዩሪ ለምርመራ ተወሰደ። ኒና፣ ልዩድቪጋ እና ዬልዬና የጉዞ እገዳ ተጣለባቸው

  5. መስከረም 4, 2020

    ኢጎር የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  6. መስከረም 8, 2020

    ዬካትዬሪና የወንጀል ክስ ተመሠረተባት

  7. መስከረም 29, 2020

    ኤሌና ባርማኪና በተከሰሰችበት የጽንፈኝበት ወንጀል በቂ ማስረጃ ስላልቀረበ ጉዳዩ ወደ አቃቤ ሕጉ ተመለሰ

  8. ነሐሴ 11, 2021

    ዩሪ የወንጀል ክስ ተመሠረተበት። የኤሌና ባርማኪና ክስ በድጋሚ መታየት ጀመረ፤ የሁሉም ጉዳይ በአንድ የክስ ፋይል ውስጥ ተጠቃለለ

  9. መስከረም 28, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

a b የእህት ኒና አስትቫትስቱሮቫን እና የእህት ልዩድቪጋ ካታናዬቫን ሐሳብ ማግኘት አልተቻለም።