መስከረም 20, 2022
ሩሲያ
ጽናት ጥሩ ውጤት ያስገኛል
በቮሮኒሽ ከተማ የሚገኘው የሌቮቤርዬዥኒ አውራጃ ፍርድ ቤት ከወንድም አሌክሴ አንቲዩኪን፣ ከወንድም ሰርጌ ባዬቭ፣ ከወንድም ዩሪ ጋልካ፣ ከወንድም ቫልዬሪ ጉርስኪ፣ ከወንድም ኢጎር ፖፖቭ፣ ከወንድም ቪታሊ ኔሩሽ፣ ከወንድም ስቴፓን ፓንክራቶቭ፣ a ከወንድም ዬቭጌኒ ሶኮሎቭ፣ ከወንድም ሚካኼል ቬሴሎቭ እና ከወንድም አናቶሊ ያጉፖቭ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍባቸው የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።
የክሱ ሂደት
ሐምሌ 13, 2020
በቮሮኒሽ እና በአካባቢው የሚገኙ ከ100 በላይ የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ተፈተሹ። ከ40 የሚበልጡ ወንድሞችና እህቶች ለምርመራ ተወሰዱ። ከላይ ስማቸው የተጠቀሱት አሥር ወንድሞች ደግሞ ጣቢያ እንዲቆዩ ተደረጉ
ከሐምሌ 14-15, 2020
አሥሩም ወንድሞች ማረፊያ ቤት እንዲገቡ ተደረጉ
ከነሐሴ 3–መስከረም 18, 2020
ወንድም ሰርጌ ባዬቭ፣ ወንድም ስቴፓን ፓንክራቶቭ፣ ወንድም ኢጎር ፖፖቭና ወንድም አናቶሊ ያጉፖቭ ከማረፊያ ቤት ተለቅቀው የቁም እስረኛ ተደረጉ
ከታኅሣሥ 1-3, 2020
ወንድም አሌክሴ አንቲዩኪን፣ ወንድም ዩሪ ጋልካ፣ ወንድም ቫልዬሪ ጉርስኪ፣ ወንድም ቪታሊ ኔሩሽ፣ ወንድም ዬቭጌኒ ሶኮሎቭና ወንድም ሚካኼል ቬሴሎቭ ከማረፊያ ቤት ተለቀቁ። ሰርጌ፣ ስቴፓን፣ ኢጎርና አናቶሊ ከቁም እስር ነፃ ሆኑ
ታኅሣሥ 13, 2021
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
በሩሲያ የሚገኙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በይሖዋ በመታመን መጽናታቸው ጥሩ ውጤት እንዳስገኘላቸው ማወቃችን አበረታቶናል።—ያዕቆብ 1:4