በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ናታሊያ ቮሮፓዬቫ

ግንቦት 22, 2023
ሩሲያ

“ፍርሃት ተፈጥሯዊ ምላሽ ነው፤ ድፍረት ግን የምርጫ ጉዳይ ነው”

“ፍርሃት ተፈጥሯዊ ምላሽ ነው፤ ድፍረት ግን የምርጫ ጉዳይ ነው”

በክራስናያርስክ የሚገኘው የዠለዝኖዶሮዥኒ አውራጃ ፍርድ ቤት መጋቢት 24, 2023 በእህት ናታሊያ ቮሮፓዬቫ ላይ ብይን አስተላልፏል። እህታችን 360,000 ሩብል (4,730 የአሜሪካ ዶላር) የገንዘብ መቀጮ እንዲጣልባት ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

አጭር መግለጫ

እንደ ናታሊያ ሁሉ እኛም “በሙሉ ልብ ‘ይሖዋ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም’” እንላለን።—ዕብራውያን 13:6

የክሱ ሂደት

  1. ከኅዳር 2017–ኅዳር 2020

    ክትትል ይደረግባት ጀመር፤ መኖሪያ ቤቷ ተፈተሸ። በወንድም አንድሬ ስቱፕኒኮቭ ላይ ከሚደረገው የወንጀል ምርመራ ጋር ተያይዞ ምርመራ ተደረገባት

  2. መስከረም 5, 2022

    የክስ ፋይል ተከፈተባት

  3. መስከረም 6, 2022

    የጉዞ ክልከላዎች ተጣሉባት

  4. ጥቅምት 20, 2022

    በወንጀል ተከሰሰች

  5. የካቲት 27, 2023

    ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  6. መጋቢት 24, 2023

    ፍርድ ቤቱ 360,000 ሩብል (4,730 የአሜሪካ ዶላር) የገንዘብ መቀጮ ጣለባት