በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ግንቦት 15, 2023
ሩዋንዳ

በምዕራባዊ ሩዋንዳ የጣለው ዶፍ ዝናብ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት አስከተለ

በምዕራባዊ ሩዋንዳ የጣለው ዶፍ ዝናብ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት አስከተለ

ግንቦት 2 እና 3, 2023 በምዕራባዊ ሩዋንዳ የጣለው ዶፍ ዝናብ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት እንዲፈጠር አድርጓል። ይህ አደጋ ከ130 የሚበልጡ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩም ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። ጎርፉና የመሬት መንሸራተቱ ሰብልን፣ ቤቶችን፣ ድልድዮችንና መንገዶችን አውድሟል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣም ሆነ የተጎዳ የለም

  • 51 ቤቶች ወድመዋል

  • 43 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 2 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የእርዳታ ሥራውን ለማስተባበርና አስፈላጊውን እገዛ ለማድረግ 3 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል

  • የቅርንጫፍ ኮሚቴ አባላት፣ የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው ያሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች አደጋው በደረሰበት አካባቢ ላሉት ወንድሞች መንፈሳዊ ማበረታቻ እየሰጡ ነው

ይሖዋ “በጭንቅ” ላይ ያሉትን የሩዋንዳ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን መደገፉን እንዲቀጥል እንጸልያለን።—መዝሙር 46:1