በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥር 18, 2023
ሰሜን መቄዶንያ

የማቴዎስ መጽሐፍ በሮማኒ (መቄዶንያ) ቋንቋ ወጣ

የማቴዎስ መጽሐፍ በሮማኒ (መቄዶንያ) ቋንቋ ወጣ

የሰሜን መቄዶንያ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ዳንኤል ጆቫኖቪች ጥር 8, 2023 እንዳበሰረው መጽሐፍ ቅዱስ—የማቴዎስ ወንጌል በሮማኒ (መቄዶንያ) ቋንቋ በሲሪሊክ እና በሮማን የፊደል አጣጣል ወጥቷል።

መጽሐፉ መውጣቱ የተነገረው ሰሜን መቄዶንያ፣ ስኮፕዬ ውስጥ በተካሄደ ልዩ የቀጥታ ፕሮግራም ላይ ነው። በማዕከላዊ አውሮፓ ቅርንጫፍ ቢሮ ክልል የሚገኙ ሁሉም የሮማኒ (መቄዶንያ) ጉባኤዎችና ቡድኖች ፕሮግራሙን በ​JW ስትሪም-ስቱዲዮ አማካኝነት ከያሉበት ሆነው እንዲከታተሉ ተጋብዘው ነበር። መጽሐፉ መውጣቱ እንደተበሰረ በዲጂታልና በድምፅ ፎርማቶች ተለቅቋል። በስብሰባው ላይ በአካል የተገኙት ደግሞ በሲሪሊክ የፊደል አጣጣል የታተመውን ቅጂ አግኝተዋል።

የሮማኒ የቋንቋ ቤተሰብ የተለያዩ ቀበሌኛዎች አሉት። a የይሖዋ ምሥክሮች በሮማኒ (መቄዶንያ) ቋንቋ ጽሑፎችን በቋሚነት መተርጎም የጀመሩት በ2007 ነው። በአሁኑ ወቅት የትርጉም ቡድኑ ሥራውን የሚያከናውነው ስኮፕዬ ባለው ቅርንጫፍ ቢሮ ሆኖ ነው፤ ስኮፕዬ፣ ሰሜን መቄዶንያ ውስጥ አብዛኞቹ የሮማኒ (መቄዶንያ) ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚኖሩባት ከተማ ናት።

የሮማኒ (መቄዶንያ) ቋንቋ የትርጉም ቡድን የሚሠራው በሰሜን መቄዶንያ፣ ስኮፕዬ ባለው ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ ነው

አንድ ወንድም እንዲህ ብሏል፦ “ይህን ትርጉም በገዛ ቋንቋዬ ሳነብ ይሖዋ በግል የሚያናግረኝ ያህል ሆኖ ነው የሚሰማኝ።”

አንድ ሌላ ወንድምም እንዲህ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፦ “የማቴዎስ መጽሐፍን ሳነብ ኢየሱስ ለአድማጮቹ ያስተላለፈው ሐሳብ ፍንትው ብሎ ይታየኛል።”

ይህ መጽሐፍ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ‘የመንግሥቱን ምሥራች ሲሰብኩ’ ውጤታማ እንዲያደርጋቸው እንጸልያለን።—ማቴዎስ 9:35