በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ግንቦት 12, 2023
ሱዳን

በሱዳን የተቀሰቀሰው ከባድ ውጊያ እንደቀጠለ ነው

በሱዳን የተቀሰቀሰው ከባድ ውጊያ እንደቀጠለ ነው

ሚያዝያ 15, 2023 የሱዳን ዋና ከተማ በሆነችው በካርቱም በሁለት ታጣቂ ቡድኖች መካከል ውጊያ ተቀሰቀሰ። የዜና ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት በውጊያው ከ600 የሚበልጡ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ 5,000 ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • በካርቱም ካለው ጦርነት የሸሹ ወንድሞችና እህቶች በሱዳን፣ ወድ መደኒ ከተማ ውስጥ መንፈሳዊ ማበረታቻ ለማግኘት ተሰብስበው

    ከወንድሞቻችንና እህቶቻችን መካከል ጉዳት የደረሰበት ወይም ሕይወቱን ያጣ የለም

  • ቢያንስ 318 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። አንዳንዶች ወደ አጎራባች አገራት ሸሽተዋል

  • 8 አዋቂዎችና 5 ልጆች ለተወሰነ ጊዜ ያህል ከሥራ ቦታቸውና ከትምህርት ቤታቸው መውጣት አልቻሉም ነበር። አሁን ሁሉም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የጉባኤ ሽማግሌዎች በአካባቢው ያሉትን ወንድሞችና እህቶች እያበረታቱ ነው

  • የእርዳታ እንቅስቃሴውን ለማስተባበርና አስፈላጊውን እርዳታ ለመስጠት በሱዳንና በአጎራባች አገራት የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል

‘ሰላም የሚበዛበትን’ ጊዜ በጉጉት እየተጠባበቅን በዚህ ውጊያ ሕይወታቸው ለተቃወሰባቸው ወንድሞቻችን መጸለያችንን እንቀጥላለን።—መዝሙር 72:7