በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ነሐሴ 14, 2019
ስሎቫኪያ

በሮማኒ ቋንቋ (ምሥራቅ ስሎቫኪያ) የመጀመሪያው የክልል ስብሰባ ተካሄደ

በሮማኒ ቋንቋ (ምሥራቅ ስሎቫኪያ) የመጀመሪያው የክልል ስብሰባ ተካሄደ

በስብሰባው ላይ ከተጠመቁት 19 ሰዎች መካከል አንዷ

በስሎቫኪያ የሚኖሩ ወንድሞቻችን ሐምሌ 20 እና 21, 2019 በሮማኒ ቋንቋ የመጀመሪያውን የክልል ስብሰባ በሚኻሎቭትሴ ዊንተር ስታዲየም አደረጉ። በዚህ የሁለት ቀን ስብሰባ ላይ ከፍተኛው የተሰብሳቢዎች ቁጥር 1,276 ነበር። በድምሩ 19 ሰዎች በስብሰባው ላይ ተጠምቀዋል።

ከአራት አገሮች ማለትም ከቤልጅየም፣ ከቼክ ሪፑብሊክ፣ ከብሪታንያ እና ከዩክሬን የመጡ ወንድሞችና እህቶች በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል። ተሰብሳቢዎቹ የኢዮስያስ ታሪክ፦ ይሖዋን ውደዱ፤ ክፉ የሆነውን ነገር ጥሉ የተባለውን ፊልም በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማየት በመቻላቸው በጣም ተደስተው ነበር።

በስሎቫኪያ የመጀመሪያው የሮማኒ ቋንቋ ጉባኤ የተቋቋመው ኅዳር 2014 ነበር፤ የመጀመሪያው ጉባኤ በተቋቋመ በአምስት ዓመት ውስጥ የክልል ስብሰባ ማድረግ ተችሏል። በአሁኑ ወቅት በቼክ-ስሎቫክ ቅርንጫፍ ቢሮ ክልል ውስጥ በሮማኒ ቋንቋ የሚመሩ 9 ጉባኤዎች፣ 10 ቡድኖችና 14 ቅድመ ቡድኖች አሉ።

የስታዲየሙ ኃላፊ የሆነው ፒተር ቲርፔክ እንዲህ ብሏል፦ “የይሖዋ ምሥክሮች ያደረጉልን ትብብር በጣም አስደናቂ ነው። ምንጊዜም ቃላችሁን ትጠብቃላችሁ። በድጋሚ ብትመጡ ደስ ይለናል።”

የክልል ስብሰባው የፕሮግራም የበላይ ተመልካች የሆነው ወንድም ፒተር ቫርጋ እንዲህ ብሏል፦ “እንዲህ ያለ ስብሰባ አይቼ አላውቅም። ይህ ስብሰባ የሮማኒ ቋንቋ ተናጋሪ ለሆኑ ውድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ታሪካዊ ስብሰባ ነበር። ተሰብሳቢዎቹ ከዚህ በፊት ተገናኝተው ባያውቁም ከመደምደሚያው መዝሙር በኋላ መተቃቀፍ ጀመሩ። ብዙዎቹ ዓይናቸው እንባ አቅርሮ ነበር።”

በስሎቫኪያ ከሚኖሩት የሮማኒ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ 1,010 አስፋፊዎች ጋር አብረን ተደስተናል። እንዲህ ያሉት ስብሰባዎች በይሖዋ ሕዝቦች መካከል ያለውን እውነተኛ ፍቅር ጎላ አድርገው ያሳያሉ።—ዮሐንስ 13:34, 35