በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ኅዳር 6, 2019
ስፔን

በምሥራቅ ስፔን የተከሰተው ኃይለኛ ጎርፍ ብዙ ጉዳት አስከተለ

በምሥራቅ ስፔን የተከሰተው ኃይለኛ ጎርፍ ብዙ ጉዳት አስከተለ

በ2019 መስከረምና ጥቅምት ወራት በምሥራቅ ስፔን ውስጥ በተደጋጋሚ የጣለው ከባድ ዝናብ ብዙ ጉዳት አስከትሏል። ከሁሉም ከባዱ አደጋ የደረሰው ጥቅምት 23 በታራጎና ግዛት ውስጥ የሚገኘው የፍራንኮሊ ወንዝ ሞልቶ ኃይለኛ ጎርፍ በተከሰተበት ወቅት ነው። የሚያሳዝነው በጎርፉ ምክንያት አምስት ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። ከሞቱት ሰዎች መካከል ሁለት ወንድሞቻችን ይገኙበታል፤ እነዚህ ወንድሞች ከጉባኤ ስብሰባ ወደ ቤታቸው ለመመለስ ድልድይ እያቋረጡ ሳለ ጎርፉ መኪናቸውን ወሰደው።

የጉባኤ ሽማግሌዎች በሁለቱ ወንድሞች ሞት ምክንያት ያዘኑትን የጉባኤው አባላት እያጽናኑ ነው። እንዲሁም የስፔን ቅርንጫፍ ቢሮ ኮሚቴ አባል የሆነ አንድ ወንድም ተጨማሪ ማጽናኛና ማበረታቻ ለመስጠት ወደዚያ ጉባኤ ሄዶ ነበር።

ይሖዋ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለፉ ያሉትን ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ማጽናናቱን እንዲቀጥል እንጸልያለን።—2 ቆሮንቶስ 1:3, 4