በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሚያዝያ 14, 2022
ስፔን

አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በካታላን ቋንቋ ወጣ

አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በካታላን ቋንቋ ወጣ

ሚያዝያ 2, 2022 የስፔን ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም አልቤርቶ ሮቪራ አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በካታላን ቋንቋ በዲጂታል ፎርማት መውጣቱን አብስሯል። በአንዶራ እንዲሁም ባሌሪክ ደሴቶችን፣ ካታሎኒያንና ቫሌንሲያን ጨምሮ በተለያዩ የስፔን ክልሎች የሚኖሩ የካታላን ተናጋሪ የይሖዋ ምሥክሮች ፕሮግራሙን በኢንተርኔት ተከታትለዋል፤ ፕሮግራሙን ለመከታተል ከ3,000 በላይ መሣሪያዎች JW ስትሪም ላይ ገብተው ነበር። የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ በቀጣዮቹ ወራት ለጉባኤዎች እንደሚደርስ ይጠበቃል።

ከ13ኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ ተርጓሚዎች መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ካታላን ሲተረጉሙ ቆይተዋል። ለየት ካሉት ትርጉሞች መካከል ከ1282 እስከ 1325 ባሉት ዓመታት ውስጥ የታተመው ቤት የሚመታ መጽሐፍ ቅዱስ ይገኝበታል። ይህ የውርስ ትርጉም 18 የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን በግጥም መልክ ይዟል፤ ይህም መልእክቱን ለማስታወስ ይረዳል።

ወንድሞችና እህቶች መጽሐፍ ቅዱሱ መውጣቱን የሚያበስረውን ንግግር በስብሰባ አዳራሻቸው ከ​JW ስትሪም ሲከታተሉ

በርካታ የካታላን ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱሶች የሚጠቀሙት ለመረዳት ከባድ የሆነ ጥንታዊ ቋንቋ ነው። ሌሎች ትርጉሞች ደግሞ የይሖዋን ስም አስወጥተዋል፤ ወይም ደግሞ ሌሎች ስህተቶች አሏቸው።

ወንድም ሮቪራ በንግግሩ ላይ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “ይህ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን ሐሳብ በአፍ መፍቻ ቋንቋችን በትክክል እንደሚያስተላልፍ እርግጠኞች ነን።”

የካታላን ተናጋሪዎች በሙሉ ኃይለኛ ከሆነው የአምላክ ቃል የተሟላ ጥቅም በማግኘታቸው በጣም ደስ ብሎናል።—ዕብራውያን 4:12