በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ቡልጋሪያ

ታሪካዊ ኩነቶች—ቡልጋሪያ

ታሪካዊ ኩነቶች—ቡልጋሪያ
  1. ግንቦት 19, 2004—የአውሮፓ ሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት፣ በከሳሽ ሎተር እና ተከሳሽ ቡልጋሪያ የክስ መዝገብ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረሰውን የመግባቢያ ውል ተቀበለው፤ መንግሥት፣ የይሖዋ ምሥክሮችን የማምለክና እምነታቸውን ያለገደብ የመናገር ሕጋዊ መብታቸውን ለማክበር ተስማማ

  2. ሚያዝያ 16, 2003—መንግሥት፣ የክርስቶስ ሞት መታሰቢያን የይሖዋ ምሥክሮች ክብረ በዓል አድርጎ በይፋ መዘገበው፤ ይህም የይሖዋ ምሥክሮች በዕለቱ ከሥራ ነፃ እንዲሆኑ ይፈቅዳል

  3. መጋቢት 6, 2003—የይሖዋ ምሥክሮች፣ የሃይማኖት ድርጅቶችን በሚመለከተው አዲስ ሕግ መሠረት ዳግመኛ ተመዘገቡ

  4. ግንቦት 3, 2001—የአውሮፓ ሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት፣ ከሳሽ ስቴፋኖቭ እና ተከሳሽ ቡልጋሪያ ያደረጉትን የመግባቢያ ውል ተቀበለው፤ የቡልጋሪያ መንግሥት፣ በወታደራዊ አገልግሎት ምትክ አማራጭ የሲቪል አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ወንድሞችን ከክስ ነፃ አደረገ

  5. ጥቅምት 7, 1998—በቡልጋሪያ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች ሕጋዊ ፈቃድ አገኙ

  6. መጋቢት 9, 1998—በአውሮፓ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (አሁን የአውሮፓ ሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ይባላል) ተቀባይነት ባገኘው የመግባቢያ ሰነድ መሠረት የቡልጋሪያ መንግሥት የይሖዋ ምሥክሮችን እንደ አንድ ሃይማኖታዊ ድርጅት ለመመዝገብ ተስማማ

  7. 1994—ቡልጋሪያ በሃይማኖት ላይ ገደብ የሚጥል ሕግ ማጽደቋን ተከትሎ የይሖዋ ምሥክሮችን ሕጋዊ ፈቃድ ሰረዘች

  8. ግንቦት 7, 1992—ቡልጋሪያ የአውሮፓ ምክር ቤት 26ኛ አባል ሆነች

  9. ሐምሌ 17, 1991—መንግሥት፣ የይሖዋ ምሥክሮች ክርስቲያናዊ ማኅበር የተሰኘውን የይሖዋ ምሥክሮች ሕጋዊ ተቋም በይፋ መዘገበ

  10. 1944-1990—በኮሚኒስት አገዛዝ ሥር የይሖዋ ምሥክሮች እንቅስቃሴ ታግዶ ቆየ

  11. ግንቦት 6, 1938—የይሖዋ ምሥክሮች ሕጋዊ እውቅና አገኙ

  12. 1888—የይሖዋ ምሥክሮች ቡልጋሪያ እንደነበሩ የሚጠቁም የመጀመሪያው መረጃ