በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቤልጅየም ያለ አንድ ቤተሰብ የ2021⁠ን የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት ሲያከብር

ሚያዝያ 16, 2021
ቤልጅየም

የ2021 የመታሰቢያው በዓል አከባበር—በቤልጅየም ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች በአሥርተ ዓመታት ውስጥ ከፍተኛውን የመታሰቢያ በዓል ተሰብሳቢዎች ቁጥር አስመዘገቡ

የ2021 የመታሰቢያው በዓል አከባበር—በቤልጅየም ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች በአሥርተ ዓመታት ውስጥ ከፍተኛውን የመታሰቢያ በዓል ተሰብሳቢዎች ቁጥር አስመዘገቡ

በ2021 በቤልጅየም በአጠቃላይ 49,040 የሚያህሉ ሰዎች የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ በዓል አክብረዋል፤ የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ የይሖዋ ምሥክሮች ከሁሉ የላቀ ቦታ የሚሰጡት ዓመታዊ በዓል ነው። በቤልጅየም ከ1995 ወዲህ በክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ ይህን ያህል ተሰብሳቢ ተገኝቶ አያውቅም። የተሰብሳቢዎቹ ቁጥር በአገሪቱ ካሉት የይሖዋ ምሥክሮች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር እጥፍ ገደማ ይሆናል።

ይህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተሰብሳቢዎች በሃይማኖታዊ ዝግጅት ላይ መገኘታቸው ትኩረት የሚስብ ነው፤ ምክንያቱም በቤልጅየም ሃይማኖት የለሽ የሆኑ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ በ1970 ከ90 በመቶ የሚበልጡ የቤልጅየም ዜጎች ክርስቲያኖች እንደሆኑ የተናገሩ ሲሆን ሃይማኖት የለሽ እንደሆኑ የተናገሩት ሰዎች ቁጥር ከ6 በመቶ ብዙም አይበልጥም ነበር። በቅርብ ጊዜ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ግን በቤልጅየም ያሉ ክርስቲያኖች ቁጥር ቀንሶ ከ60 በመቶ በታች ሆኗል። ሃይማኖት የለሽ እንደሆኑ የሚናገሩ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ40 በመቶ በላይ ደርሷል።

ባለፉት ዓመታት በቤልጅየም ያሉ የመገናኛ ብዙኃን ስለ ይሖዋ ምሥክሮች የተዛቡ አልፎ አልፎም ከእውነታው የራቁ ሪፖርቶችን ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ያም ሆኖ ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሄደ የቤልጅየም ዜጎች ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ነው። ፍላጎት ያላቸው በርካታ ሰዎች በይሖዋ ምሥክሮች መካከል ያለውን ፍቅር እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር ተግባራዊ ማድረግ የሚያስገኘውን ጥቅም መመልከት ችለዋል።—ዮሐንስ 13:35

አንዲት እህት በ2021 የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ ላይ የተገኘችን በቅርቡ የተጠመቀች እህት ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ የተባለውን መጽሐፍ ተጠቅማ ስታስጠናት

በቤልጅየም ያለው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ የካቲት 2021 ባቀረበው ሪፖርት ላይ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያጠኑ ሰዎች ቁጥር 11,804 እንደደረሰ ገልጿል፤ ይህ አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ባለፈው የአገልግሎት ዓመት ከተመዘገበው አማካይ ቁጥር በ1,000 ገደማ ይበልጣል። ላለፉት አምስት ዓመታት ያህል በየዓመቱ በአማካይ 450 የሚያህሉ ሰዎች ተጠምቀው የይሖዋ ምሥክር ሆነዋል።

በቤልጅየም እየታየ ያለው ይህ እድገት በዓለም ዙሪያ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች “ጥቂት የሆነው ሺህ፣ ትንሽ የሆነውም ኃያል ብሔር ይሆናል” የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜውን ሲያገኝ እየተመለከቱ እንደሆነ ከሚያሳዩ በርካታ ምሳሌዎች መካከል አንዱ ብቻ ነው።—ኢሳይያስ 60:22