በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ግንቦት 31, 2024
ቤኒን

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በፎን ቋንቋ ወጣ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በፎን ቋንቋ ወጣ

የምዕራብ አፍሪካ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም አብዲየል ዎሩ ግንቦት 26, 2024 የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በፎን ቋንቋ መውጣቱን አብስሯል። የመጽሐፉ መውጣት የተበሰረው በአቦሜ፣ ቤኒን በሚገኝ የትላልቅ ስብሰባዎች አዳራሽ በተዘጋጀ ልዩ ፕሮግራም ላይ ነው። በፕሮግራሙ ላይ በድምሩ 920 ወንድሞችና እህቶች በአካል ተገኝተዋል። ሌሎች 6,188 ሰዎች ደግሞ ዝግጅቱን በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተከታትለዋል። የታተመው የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ቅጂ በፕሮግራሙ ላይ ለተገኙት ሁሉ ተሰራጭቷል። በተጨማሪም የድምፅና የኤሌክትሮኒክ ቅጂውን ወዲያውኑ ማውረድ ተችሏል።

በፎን ቋንቋ በሚመሩት 84 ጉባኤዎችና ቡድኖች ውስጥ የሚያገለግሉትን ከ4,000 በላይ ወንድሞችና እህቶች ጨምሮ ቤኒን ውስጥ የሚኖሩት የፎን ቋንቋ ተናጋሪዎች ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን እንደማያንስ ይገመታል። መጽሐፍ ቅዱስ—የማቴዎስ ወንጌል በ2022 መውጣቱን ተከትሎ ተጨማሪ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ክፍሎች ደረጃ በደረጃ በዚሁ ቋንቋ በኤሌክትሮኒክ ቅጂ ሲወጡ ቆይተዋል።

ይሖዋ፣ ጥበብ በሚንጸባረቅበት ምክሩ መሠረት ሕይወታቸውን መምራት ለሚፈልጉ ብዙ ሰዎች እውነት የሆነው ቃሉ እንዲዳረስ ስላደረገ እኛም ከፎን ቋንቋ ተናጋሪ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር በመሆን እናመሰግነዋለን።​—ዮሐንስ 17:17