በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሐምሌ 18, 2019
ብራዚል

ሳኦ ፓውሎ፣ ብራዚል—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ

ሳኦ ፓውሎ፣ ብራዚል—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
  • ቀን፦ ከሐምሌ 12-14, 2019

  • ቦታ፦ በሳኦ ፓውሎ፣ ብራዚል የሚገኘው ሳኦ ፓውሎ ኤክስፖ

  • ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ስፓንኛ፣ እንግሊዝኛ፣ የብራዚል ምልክት ቋንቋ፣ ጣሊያንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ፖርቱጋልኛ

  • ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 36,624

  • አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 291

  • ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 7,000

  • የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ሞዛምቢክ፣ ሱሪናም፣ ስካንዲኔቪያ፣ ቤልጅየም፣ ትሪኒዳድ እና ቶቤጎ፣ ቼክ ስሎቫክ፣ አርጀንቲና፣ አንጎላ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ፖርቱጋል፣ ቬኔዙዌላ

  • ተሞክሮ፦ ልዑካኑን አስተናግዶ የነበረው የሳኦ ፓውሎ መካነ አራዊት የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪ የሆነችው ማሪያ ሊዊዛ ጎንዛሌዝ እንዲህ ብላለች፦ “እዚህ መካነ አራዊት ውስጥ ብዙ ዝግጅቶች ተደርገው ያውቃሉ። ዓመቱን ሙሉ ቱሪስቶች ይመጣሉ፤ ሆኖም እንዲህ ያለ ብዙ ሰው የያዘ፣ አፍቃሪና የተደራጀ ቡድን አይቼ አላውቅም። በጣም አፍቃሪ ሰዎች ናችሁ! ስትተቃቀፉ፣ አብራችሁ ጊዜ ስታሳልፉና ስትዘምሩ ፍቅራችሁ በግልጽ ይታያል።”

 

የአካባቢው ወንድሞችና እህቶች በሳኦ ፓውሎ ጓሩሉስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ልዑካኑን ሲቀበሉ

ከሳኦ ፓውሎ እና ከብራዚል ቅርንጫፍ ቢሮ የመጡ አራት ወንድሞች ብሔራት አቀፍ ስብሰባው ከመደረጉ በፊት ስብሰባውን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ

ልዑካኑ ከአካባቢው አስፋፊዎች ጋር በሳኦ ፓውሎ ሲሰብኩ

ልዑካኑ በስብሰባው የመጀመሪያ ቀን በመሰብሰቢያ ቦታው ሆነው

ወንድሞችና እህቶች ስብሰባው ሲደረግ ማስታወሻ እየጻፉ

የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ሳሙኤል ኸርድ የዓርቡን ስብሰባ የመጨረሻ ንግግር ሲያቀርብ

ቅዳሜ ዕለት የተከናወነ የጥምቀት ፕሮግራም

እህቶች ማየትና መስማት ለተሳናቸው ተሰብሳቢዎች በታክታይል ምልክት ቋንቋ ሲያስተረጉሙ

ልዑካኑ ከመሰብሰቢያ አዳራሹ ውጭ ፎቶግራፍ ሲነሱ

ልዑካን ሆነው የመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እሁድ ቀን ስብሰባው ሲያልቅ ሕዝቡን ሲሰናበቱ