ጥር 4, 2022
ብራዚል
በሰሜን ምሥራቅ ብራዚል የጣለው ከባድ ዝናብ ጎርፍ አስከትሏል
ከታኅሣሥ 24 እስከ 26, 2021 በባህያ ግዛት፣ ብራዚል ከባድ ዝናብ የጣለ ሲሆን ከ640,000 በላይ ሰዎች በጎርፉ ተጎድተዋል። ጎርፉ ግድቦችን አፍርሷል። በዚህም ምክንያት በርካታ ከተሞች ተጥለቅልቀዋል፤ ነዋሪዎቻቸውም አካባቢዎቹን ለቀው ወጥተዋል።
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
ከወንድሞቻችን መካከል አካላዊ ጉዳት የደረሰበት የለም
273 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
109 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
3 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል፤ ኮሚቴው ውኃ፣ ምግብና ልብስ እያቀረበ ነው
ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ አስፋፊዎች ዘመዶቻቸው ወይም ሌሎች አስፋፊዎች ጋ ጊዜያዊ መጠለያ አግኝተዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴው በሙሉ የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው
በአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴው ውስጥ የሚያገለግለው ወንድም ማርሴሎ አምብሮሲዮ እንዲህ ብሏል፦ “የወንድማማች ፍቅር በተግባር ሲገለጽ በማየታችን በጣም ተበረታተናል፤ ይሖዋን ከበፊቱ የበለጠ ለማገልገል ያለን ቁርጠኝነትም ተጠናክሯል።”
ይሖዋ በጎርፉ ለተጎዱ ወንድሞቻችን “አስተማማኝ መጠጊያ” እንደሚሆንላቸው እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 9:9