በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ታኅሣሥ 28, 2020
ብራዚል

በሳንታ ካታሪና፣ ብራዚል የተከሰተ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት

በሳንታ ካታሪና፣ ብራዚል የተከሰተ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት

ቦታ

በሳንታ ካታሪና፣ ደቡባዊ ብራዚል የሚገኘው የቫሊ ዶ ኢታዣይ ክልል

የደረሰው አደጋ

  • ከሐሙስ፣ ታኅሣሥ 17, 2020 አንስቶ የጣለው ከባድ ዝናብ መጠነ ሰፊ ጉዳትና የመሬት መንሸራተት አስከትሏል

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 22 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • የሚያሳዝነው አንዲት የ65 ዓመት እህት ቤታቸው በመሬት መንሸራተት በመደርመሱ ሕይወታቸው አልፏል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 15 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ የወረዳ የበላይ ተመልካቹ እንዲሁም የጉባኤ ሽማግሌዎች ሕይወታቸው ያለፈውን እህት ቤተሰቦች ጨምሮ በአደጋው የተጎዱትን ሁሉ እያጽናኑ እና እየደገፉ ነው

  • የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴው በአካባቢው ያሉትን ወንድሞች በማስተባበር፣ ጉዳት የደረሰባቸውን ከተሞች ጎብኝተው ምን ዓይነት እርዳታ እንደሚያስፈልግ እንዲገመግሙ እንዲሁም በጎርፍ የተጥለቀለቁትን ቤቶች በማጽዳቱ ሥራ እንዲያግዙ አድርጓል። በተጨማሪም ኮሚቴው ምግብና ከ2,000 ሊትር በላይ የመጠጥ ውኃ ለአስፋፊዎቹ እንዲደርስ ዝግጅት አድርጓል። ሁሉም የእርዳታ ሥራዎች እየተከናወኑ ያሉት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

በዚህ አደጋ ምክንያት እህታችንን በማጣታችን በጣም አዝነናል። የተፈጥሮ አደጋም ሆነ ‘ሞት የማይኖርበትን’ ጊዜ በጉጉት እንጠብቃለን።—ራእይ 21:4