በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ኃይለኛ ዝናብና የመሬት መንሸራተት ተራራማ ከተማ በሆነችው በፔትሮፖሊስ ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል

የካቲት 23, 2022
ብራዚል

ከባድ ዝናብና የመሬት መንሸራተት በብራዚል በሚገኝ ተራራማ ከተማ ላይ ውድመት አስከተለ

ከባድ ዝናብና የመሬት መንሸራተት በብራዚል በሚገኝ ተራራማ ከተማ ላይ ውድመት አስከተለ

የካቲት 15, 2022 በብራዚል፣ በሪዮ ዴ ጄኔሮ ግዛት በምትገኘው በተራራማዋ የፔትሮፖሊስ ከተማ ከባድ ዝናብ በመጣሉ የመሬት መንሸራተት ተከሰተ። አደጋው መኖሪያ ቤቶችንና የንግድ ቦታዎችን አውድሟል። በ24 ሰዓት ውስጥ 26 ሴንቲ ሜትር የሚያክል ዝናብ ጥሏል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 1 ወንድም ከባድ ጉዳት ደርሶበት በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል ተወስዷል። የሚያሳዝነው የ2 ዓመት ልጁ በመሬት መንሸራተቱ ምክንያት ሕይወቱን አጥቷል

  • 1 ሌላ ወንድምም ሞቷል

  • 86 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 2 ቤቶች ፈርሰዋል

  • 15 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 2 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የእርዳታ ሥራውን ለማደራጀት የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች በአደጋው ለተጎዱ ወንድሞች ምግብ፣ ውኃ እና አልባሳት በማቅረብ እንዲሁም መንፈሳዊ ማበረታቻ በመስጠት እርዳታ እያደረጉላቸው ነው

  • ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉት ወንድሞችና እህቶች ለጊዜው ከዘመዶቻቸውና ከሌሎች የይሖዋ ምሥክሮች ጋር እየኖሩ ነው

  • የእርዳታ ሥራው በሙሉ እየተከናወነ ያለው ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች በተከተለ መልኩ ነው

በአደጋው ለተጎዱት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንጸልያለን። ይሖዋ በተለይ የሚወዷቸውን ሰዎች በሞት ያጡትን ‘ልባቸውን እንደሚያጽናና እና እንደሚያጸናቸው’ ሙሉ እምነት አለን።—2 ተሰሎንቄ 2:16, 17