በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በሪሲፊ ሲቲ፣ ፔርናምቡኮ ግዛት፣ ብራዚል የሚገኘው የትላልቅ ስብሰባ አዳራሽ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል

ሰኔ 10, 2022
ብራዚል

ጎርፍና የመሬት መንሸራተት በብራዚል ከባድ ጉዳት አደረሰ

ጎርፍና የመሬት መንሸራተት በብራዚል ከባድ ጉዳት አደረሰ

ግንቦት 25, 2022 በሰሜናዊ ብራዚል የጣለው ከባድ ዝናብ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት አስከትሏል። በአደጋው በጣም የተጎዱት የአላጎኧስ እና የፔርናምቡኮ ግዛቶች ሲሆኑ በዚያ ያሉ 42 ከተሞች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። ከ145,000 የሚበልጡ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፤ ቢያንስ 129 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ከወንድሞቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ የለም

  • 3 አስፋፊዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 280 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 22 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 23 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 የትላልቅ ስብሰባ አዳራሽ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ከ600 ለሚበልጡ አስፋፊዎች መሠረታዊ ነገሮችንና መንፈሳዊ ማበረታቻ ለመስጠት ጥረት እያደረገ ነው

  • የእርዳታ እንቅስቃሴው በሙሉ የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

በዚህ የተፈጥሮ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወንድሞቻችን ‘ከጌታና ከታላቅ ብርታቱ ኃይል ማግኘታቸውን እንዲቀጥሉ’ እንጸልያለን።—ኤፌሶን 6:10