በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሰኔ 3, 2019
ቦሊቪያ

በቦሊቪያ የተከሰተ የመሬት መንሸራተት የላ ፓዝን የተወሰነ ክፍል አወደመ

በቦሊቪያ የተከሰተ የመሬት መንሸራተት የላ ፓዝን የተወሰነ ክፍል አወደመ

በሚያዝያ 30, 2019 የተከሰተው የመሬት መንሸራተት በላ ፓዝ የሚገኘውን የሳን ሆርሄ ካንቱታኒ አብዛኛውን ክፍል አወደመ። በዚህም ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።

የቦሊቪያ ቅርንጫፍ ቢሮ ሪፖርት እንዳደረገው በአደጋው ሕይወቱን ያጣ ወይም የአካል ጉዳት የደረሰበት የይሖዋ ምሥክር ባይኖርም ሁለት የይሖዋ ምሥክር ቤተሰቦች ቤታቸው ሙሉ በሙሉ ወድሟል። ከዚህ ውጭ ግን አደጋው በደረሰበት አካባቢ የሚኖሩ 11 የይሖዋ ምሥክር ቤተሰቦች ቢኖሩም ቤታቸው ይህ ነው የሚባል ጉዳት አልደረሰበትም።

የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴው፣ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች እንዲሁም በአካባቢው ያሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች በቅርንጫፍ ቢሮው አመራር ሥር ሆነው ለወንድሞች መንፈሳዊም ሆነ ተግባራዊ እርዳታ እያበረከቱ ነው። አደጋው በደረሰበት አካባቢ የሚኖሩት ወንድሞች ዝናብ መዝነቡን ከቀጠለ በድጋሚ የመሬት መንሸራተት ሊከሰት እንደሚችል በማሰብ ተገቢውን ጥንቃቄ እያደረጉ ነው።

በወንድሞቻችን ላይ ምንም ጉዳት ባለመድረሱ እንዲሁም የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ እያገኙ በመሆኑ አመስጋኞች ነን።—ገላትያ 6:10