በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በአደጋው የወደመ የአንዲት እህት ቤት፤ በዋና ከተማዋ በፖርት ቪላ አቅራቢያ

መጋቢት 17, 2023
ቫንዋቱ

ሁለት ኃይለኛ አውሎ ነፋሶች ቫንዋቱን አናወጧት

ሁለት ኃይለኛ አውሎ ነፋሶች ቫንዋቱን አናወጧት

በአራተኛ እርከን ሥር የሚመደቡ ሁለት ኃይለኛ አውሎ ነፋሶች ከመጋቢት 1 እስከ 4, 2023 ባሉት ቀናት በቫንዋቱ ጉዳት አድርሰዋል። ጁዲ የተባለው የመጀመሪያው አውሎ ነፋስ ያደረሰው ጉዳት እምብዛም ከባድ አልነበረም። ብዙም ሳይቆይ ግን ኬቨን የተባለው አውሎ ነፋስ በቀድሞው አውሎ ነፋስ የተመቱትን አካባቢዎች መታ። ኤፋቴ የተባለውን የአገሪቱን ዋነኛ ደሴት ጨምሮ በደቡባዊው ክፍል የሚገኙ በርካታ ደሴቶች ከፍተኛ ውድመት ደርሶባቸዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ የለም

  • 3 መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል

  • 30 መኖሪያ ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 2 የስብሰባ አዳራሾች ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው ያሉት የጉባኤ ሽማግሌዎች፣ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው እረኝነት እያደረጉና የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች እያሟሉ ነው

  • የእርዳታ ሥራውን ለማደራጀት የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል

ይህ በቫንዋቱ ላሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን አስጨናቂ ወቅት ነው፤ ያም ቢሆን ይሖዋ እነሱን ‘ማጽናናቱንና ማረጋጋቱን’ እንደሚቀጥል እንተማመናለን።—መዝሙር 94:19