በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ግንቦት 8, 2021
ቱርክሜኒስታን

ቱርክሜንስታን በተለያዩ እስር ቤቶች የነበሩ 16 ወንድሞችን ለቀቀች

ቱርክሜንስታን በተለያዩ እስር ቤቶች የነበሩ 16 ወንድሞችን ለቀቀች

ቱርክሜኒስታን ግንቦት 8, 2021 በተለያዩ እስር ቤቶች የነበሩትን 16 ወንድሞች በሙሉ ከእስር ለቅቃለች። እነዚህ ወንድሞች የታሰሩት በሕሊናቸው ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነበር። እኛም ይህን ዜና በመስማታችን ከእነዚህ ታማኝ ወንድሞችና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ደስ ብሎናል።