በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ራሱል ሮዝባዬቭ

መጋቢት 23, 2021
ቱርክሜኒስታን

የ21 ዓመቱ ወንድም ራሱል ሮዝባዬቭ በሕሊናው ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለሁለተኛ ጊዜ ተፈረደበት

የ21 ዓመቱ ወንድም ራሱል ሮዝባዬቭ በሕሊናው ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለሁለተኛ ጊዜ ተፈረደበት

የፍርድ ውሳኔ

መጋቢት 16, 2021 የቱርክሜኒስታን ፍርድ ቤት በወንድም ራሱል ሮዝባዬቭ ላይ ከተመሠረተው ክስ ጋር በተያያዘ ውሳኔውን አሳውቋል። ራሱል በሕሊናው ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ የሁለት ዓመት እስራት ተፈርዶበታል። ራሱል በገለልተኝነት አቋሙ ምክንያት ሲፈረድበት ይህ ሁለተኛ ጊዜው ነው።

አጭር መግለጫ

ራሱል ሮዝባዬቭ

  • የትውልድ ዘመን፦ 1999 (ሃላንግ)

  • ግለ ታሪክ፦ ሁለት ታላቅ እህቶችና አንድ ታናሽ ወንድም አለው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ፀጉር አስተካካይ ለመሆን ሠለጠነ። እግር ኳስና መረብ ኳስ መጫወት እንዲሁም መዋኘት ያስደስተዋል

    ወላጆቹ የይሖዋ ምሥክር የሆኑት እሱ ትንሽ ልጅ እያለ ነው። በ2013 ተጠመቀ

የክሱ ሂደት

ወንድም ራሱል ሮዝባዬቭ ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ምክንያት ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈረደበት ታኅሣሥ 19, 2017 ነበር። ለሁለት ዓመት የጉልበት ሥራ እንዲሠራ ተፈረደበት። የተወሰነ መሬት ተመድቦለት ነበር፤ በመሬቱ ላይ ስንዴ ዘርቶ የምርቱን 20 በመቶ ለመንግሥት ማስረከብ ይጠበቅበት ነበር። እርሻው የሚገኝበት ቦታ ከቤቱ በጣም ሩቅ ነበር። መኪና ስለሌለው የእርሻ ቦታው ድረስ በእግር መሄድ ነበረበት።

በቱርክሜኒስታን ሕግ መሠረት በሕሊናው ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው ለሁለተኛ ጊዜ ሊፈረድበት ይችላል። በመሆኑም ሚያዝያ 22, 2020 ራሱል ወደ ምልመራ ቢሮ በድጋሚ በመሄድ ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑን ገለጸ። በዚህም የተነሳ ባለሥልጣናቱ ለበርካታ ወራት ያህል ወደ ጦር ሠራዊት ቢሮ አመላልሰውታል፤ የወንጀል ምርመራ አድርገውበታል፤ የጤና ምርመራ እንዲያደርግ አስገድደውታል፤ እንዲሁም ክስ እንደሚመሠርቱበት አስፈራርተውታል። በመጨረሻም ጥር 22, 2021 ጉዳዩ ወደ አቃቤ ሕግ ተመራ።

ራሱል ከእሱ ጋር ተመሳሳይ ፈተና ያጋጠማቸው ወንድሞችና እህቶች ከተዉት ምሳሌ መማሩ ድፍረት ሰጥቶታል። እንዲህ ብሏል፦ “የእነሱ ምሳሌ በይሖዋ እንድታመን ረድቶኛል፤ . . . እንዲሁም በፈተና ውስጥ እንድጸና ብርታት ሰጥቶኛል። ታማኝ ሆኜ ከጸናሁ ይሖዋንና ኢየሱስን ማስደሰት እችላለሁ።” በራሱል ላይ የደረሰው ስደት የቤተሰቡም እምነት እንዲፈተን አድርጓል። እናቱ በዚህ ወቅት ምን እንዳበረታታት ስትናገር እንዲህ ብላለች፦ “የመጽሐፍ ቅዱስን ምሳሌዎች እንዲሁም በቪዲዮዎቻችን ላይ የሚወጡትን ተሞክሮዎች ስመለከት እንዲህ ያለ ፈተና ያጋጠመኝ እኔ ብቻ እንዳልሆንኩ ተገነዘብኩ። ሌሎች ወንድሞችና እህቶችም ተመሳሳይ ፈተና አጋጥሟቸዋል፤ ፈተናውንም በድል ተወጥተዋል። የእነሱ ምሳሌ እኔም እንድጸና ብርታት ሰጥቶኛል።”

በተለይ በመዝሙር 37:23, 24 ላይ የሚገኘው ሐሳብ ራሱልን አጽናንቶታል። እሱም ሆነ ሌሎቹ ደፋር ወጣት ወንድሞቻችን በይሖዋ እርዳታ እምነታቸውን፣ ታማኝነታቸውንና ደስታቸውን ጠብቀው መጽናት እንደሚችሉ እንተማመናለን።