በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ነሐሴ 20, 2019
ታይላንድ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በሌኦሽኛ ወጣ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በሌኦሽኛ ወጣ

ነሐሴ 16, 2019 በኖንግ ካይ፣ ታይላንድ በተደረገ የክልል ስብሰባ ላይ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በሌኦሽኛ መውጣቱ ተገለጸ። የታይላንድ ቅርንጫፍ ቢሮ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ፕላኮርን ፔስታንዬ በክልል ስብሰባው የመጀመሪያ ቀን ላይ መጽሐፍ ቅዱሱ መውጣቱን አብስሯል።

ሦስት አባላት ያሉት የትርጉም ቡድን ሥራውን ለመጨረስ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ገደማ ወስዶበታል። አንደኛው ተርጓሚ እንዲህ ብሏል፦ “የሌኦሽኛ ተናጋሪዎች በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው በሚጠቀሙበት ቋንቋ የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ለማስቀመጥ ተሞክሯል፤ በሌላ በኩል ደግሞ በበኩረ ጽሑፉ ላይ ያለውን ሐሳብ በትክክል የሚያስተላለፍ የትርጉም ሥራ ነው። በመሆኑም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ‘የአምላክን ጥልቅ ነገሮች’ መረዳት ይችላሉ።”—ኢዮብ 11:7

መጽሐፍ ቅዱሱ ለጥናት የሚረዱ በርካታ ጠቃሚ መሣሪያዎች አሉት፤ ለምሳሌ አንባቢዎች ጥቅሶችን በቀላሉ እንዲያገኙ የሚረዳ የቃላት ማውጫ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጾችን ትርጉም የሚያብራራ የቃላት መፍቻ አለው። በፕሮጀክቱ የተካፈለ ሌላ ተርጓሚ ደግሞ እንዲህ ብሏል፦ “በዚህ ትርጉም ተጠቅመን ስናስተምር የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻችን አስፈላጊ ነጥቦችን ከበፊቱ ይበልጥ በቀላሉ መረዳት ይችላሉ፤ እንዲሁም ልባቸው ስለሚነካ ከይሖዋ ጋር የግል ዝምድና መመሥረት ይችላሉ።”

በሌኦሽኛ የተዘጋጀው የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም ሌኦሽኛ የሚናገሩ ወንድሞችና እህቶች “ለማንኛውም መልካም ሥራ በሚገባ በመታጠቅ ሙሉ በሙሉ ብቁ” ሆነው እንዲገኙ እንደሚረዳቸው እንተማመናለን።—2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17