በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጋቢት 19, 2021
ታጂኪስታን

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚቴ ወንድም ሻሚል ካኪሞቭ ለየት ያለ አስተያየት እንዲደረግለት ጠየቀ

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚቴ ወንድም ሻሚል ካኪሞቭ ለየት ያለ አስተያየት እንዲደረግለት ጠየቀ

መጋቢት 19, 2021 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚቴ፣ የታጂኪስታን ባለሥልጣናት የ70 ዓመት አረጋዊ የሆነውን የወንድም ሻሚል ካኪሞቭን ጤንነት ለመጠበቅ ለየት ያለ አስተያየት እንዲያደርጉ ጠይቋል። ታማሚ የሆነው ወንድማችን እምነቱን በሰላማዊ መንገድ በመከተሉ ምክንያት ከየካቲት 2019 ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛል። የወንድም ሻሚል ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚቴ ታይቶ እልባት እስኪያገኝ ባለው ጊዜ ወንድም ሻሚል የተሟላ ሕክምና ወደሚያገኝበት የሕክምና ተቋም እንዲወሰድ እንዲሁም ከእስር እንዲለቀቅና ቅጣቱ በአማራጭ አገልግሎት እንዲለወጥ ኮሚቴው የታጂኪስታን ባለሥልጣናትን ጠይቋል።