ጥር 7, 2021
ታጂኪስታን
የታጂኪስታን ወታደራዊ ፍርድ ቤት በወንድም ሩስታምጆን ኖሮቭ ላይ የሦስት ዓመት ተኩል እስር ፈረደበት
ጥር 7, 2021 የታጂኪስታን ወታደራዊ ፍርድ ቤት በወንድም ሩስታምጆን ኖሮቭ ላይ የሦስት ዓመት ተኩል እስር ፈረደበት፤ ወንድም ሩስታምጆን የተፈረደበት በሕሊናው ምክንያት በወታደራዊ አገልግሎት ለመካፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ የተነሳ ነው።
ወንድም ሩስታምጆን ውሳኔው ከመተላለፉ ጥቂት ቀደም ብሎ ለፍርድ ቤቱ ሐሳቡን የመግለጽ አጋጣሚ ተሰጥቶት ነበር። ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በርካታ ጥቅሶችን በመጥቀስ ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆነበትን ምክንያት በድፍረት አስረድቷል። በተጨማሪም በአቋሙ እንዲጸና የረዳው ምን እንደሆነ ተናግሯል።
ወንድም ሩስታምጆን “ኃይልን በሚሰጠኝ በእሱ አማካኝነት ለሁሉም ነገር የሚሆን ብርታት አለኝ” የሚለውን ፊልጵስዩስ 4:13ን ጠቅሷል። በተጨማሪም እንዲህ ብሏል፦ “አምላኬ ይሖዋ በዚህ ጊዜ ሁሉ ተስፋ እንዳልቆርጥ ወይም እንዳልፈራ ከዚህ ይልቅ ደስተኛ ሆኜ እንድጸና ከአጠገቤ ሆኖ ብርታት እንደሰጠኝ እርግጠኛ ነኝ። በዚህ መንገድ ስለረዳኝ ላመሰግነው እወዳለሁ፤ ከእሱ ምሥክሮች እንደ አንዱ በመቆጠሬ ኩራት ይሰማኛል።”