በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ታኅሣሥ 2, 2019
ቶጎ

በቶጎ የደረሰ የጎርፍ መጥለቅለቅ

በቶጎ የደረሰ የጎርፍ መጥለቅለቅ

በ2019 የክረምት ወቅት የዘነበው ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ከባድ ዝናብ በሎሜ፣ ቶጎ በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከትሏል። በሰባት ጉባኤዎች ውስጥ የሚገኙ 257 ወንድሞች በጎርፉ ምክንያት ችግር ደርሶባቸዋል። ለተጎጂዎቹ እርዳታ ለማበርከት ጥረት እየተደረገ ነው።

በአንዳንዶቹ ቦታዎች ሕንፃዎች ውስጥ የገባው ውኃ ከፍታ አንድ ሜትር በመድረሱ 51 ወንድሞችና እህቶች ቤታቸውን ለቀው ለመውጣት ተገደዋል። በአቅራቢያው የሚኖሩ አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉትን ወንድሞች በቤታቸው ተቀብለው እያስተናገዱ ነው።

የጎርፉ ውኃ አንዳንዶቹን የከተማዋ የውኃ ማጠራቀሚያዎች በክሏቸዋል። በቶጎ ያለውን የይሖዋ ምሥክሮች እንቅስቃሴ የሚከታተለው የቤኒን ቅርንጫፍ ቢሮ ኮሚቴ፣ በወረዳ የበላይ ተመልካቹና በጉባኤ ሽማግሌዎች አማካኝነት የእርዳታ ቁሳቁስ እንዲሰራጭ ዝግጅት አድርጓል። ከእርዳታ ቁሳቁሶቹ መካከል የውኃ ማጣሪያ ኪኒን፣ ጀርም የሚገድል ኬሚካልና በረኪና ይገኙበታል።

በቶጎ የሚኖሩ ወንድሞቻችን አንዳቸው ለሌላው ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅር ለማሳየት በሚያደርጉት ጥረት ይሖዋ እንዲባርካቸው እንጸልያለን።—ዮሐንስ 13:34, 35