የካቲት 13, 2024
ቺሊ
ሰደድ እሳት በቺሊ የቫልፓራይሶ ክልል ውድመት አደረሰ
የካቲት 2, 2024 በቺሊ የባሕር ዳርቻ፣ በቫልፓራይሶ ክልል ኃይለኛ ነፋስና ከፍተኛ ሙቀት ያባባሳቸው ሁለት ሰደድ እሳቶች ተከስተዋል። ብዙ ነዋሪዎች በሚገኙባት ቢኛ ዴል ማር ከተማ ውስጥና ዙሪያ ያሉ ከ15,000 በላይ ቤቶች በእሳቱ ወድመዋል። አደጋው 40,000 የሚሆኑ ሰዎችን እንደነካ ይገመታል። ብዙዎች አሁንም ኤሌክትሪክና ውኃ ተቋርጦባቸዋል። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አደጋው ወደደረሰባቸው አንዳንድ አካባቢዎች መድረስ አልቻሉም። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ሪፖርት ተደርጓል። ከ130 በላይ ሰዎች ሞተዋል።
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
የሚያሳዝነው፣ 1 እህት ሞታለች
1 ወንድም ከባድ ጉዳት ደርሶበታል
24 ወንድሞችና እህቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
715 ወንድሞችና እህቶች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
72 ቤቶች ወድመዋል
2 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
1 ቤት ቀላል ጉዳት ደርሶበታል
ጉዳት የደረሰበት የስብሰባ አዳራሽ የለም
አደጋው በደረሰበት አካባቢ 4,700 ገደማ ወንድሞችና እህቶች አሉ
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የእርዳታ እንቅስቃሴዎችን የሚያስተባብር አንድ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል
የቺሊ ቅርንጫፍ ቢሮ አደጋው በደረሰበት አካባቢ ያሉ ወንድሞችና እህቶችን እንዲያበረታቱ ተወካዮች ልኳል። የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና ሽማግሌዎችም ጉዳት የደረሰባቸውን በመንፈሳዊም በቁሳዊም እያገዙ ነው
ይሖዋ በዚህ ሰደድ እሳት የተጎዱትን ሁሉ ‘ችግርና መከራ’ እንደሚመለከትና በቅርቡ የተፈጥሮ አደጋዎችን ለዘለቄታው እንደሚያስወግድ ሙሉ እምነት አለን።—መዝሙር 10:14