በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቺሊ የሚገኙ ዶኒሁዌ (በስተ ግራ) እና ሊናሬስ (በስተ ቀኝ) የተባሉ አካባቢዎች በጎርፍ ተጥለቅልቀው

ሐምሌ 6, 2023
ቺሊ

በቺሊ የተከሰተው ከባድ ጎርፍ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት አመሳቀለ

በቺሊ የተከሰተው ከባድ ጎርፍ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት አመሳቀለ

ከሰኔ 22 እስከ 25, 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ በደቡባዊ እና በማዕከላዊ ቺሊ ከ58 ሴንቲ ሜትር የሚበልጥ ከፍተኛ ዝናብ ጥሏል። ጎርፉ ወደ 20,000 የሚጠጉ ሰዎች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ላይ ጉዳት አድርሷል። ጎርፍ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ከ5,000 የሚበልጡ ቤቶች ተጎድተዋል ወይም ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ እየተደረጉ ነው። ሁለት ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ የተረጋገጠ ሲሆን ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል የተጎዳ ወይም የሞተ የለም

  • 212 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 13 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 38 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • የተጎዳ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ቲኦክራሲያዊ ሕንፃ የለም

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • በመቶዎች የሚቆጠሩ ፈቃደኛ ሠራተኞች የተጎዱትን ቤቶች በማጽዳቱና በመጠገኑ ሥራ እያገዙ ነው

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው ያሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች በአደጋው የተጎዱትን ሰዎች በመንፈሳዊ እያበረታቱና ቁሳዊ እገዛ እያደረጉላቸው ነው

  • የእርዳታ እንቅስቃሴውን የሚከታተሉ 2 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል

ይሖዋ በቺሊ ላሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ማጽናኛና ማበረታቻ መስጠቱን በመቀጠል የደረሰባቸውን አደጋ ለመቋቋም እንዲረዳቸው እንጸልያለን።—2 ተሰሎንቄ 2:16, 17