በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የኒባስ ከተማን ሰደድ እሳት ሲያጋያት፣ ኒውብሌ ግዛት

የካቲት 17, 2023
ቺሊ

አውዳሚ ሰደድ እሳት በማዕከላዊ ቺሊ ከፍተኛ ውድመት አስከተለ

አውዳሚ ሰደድ እሳት በማዕከላዊ ቺሊ ከፍተኛ ውድመት አስከተለ

ቺሊ አሥር ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ሰደድ እሳት እያንገበገባት ነው። ከየካቲት 2023 ወዲህ በመላ አገሪቱ ከ300 በላይ የእሳት ቃጠሎዎች እንደነበሩ ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል። አንድ አምስተኛ ገደማ የሚሆኑትን እስካሁን በቁጥጥር ሥር ማዋል አልተቻለም። በአገሪቱ ማዕከላዊ ክፍል በሚገኙት በአራውኬንያ፣ በቢዮቢዮ እና በኒውብሌ ግዛቶች ከ430,000 ሄክታር የሚበልጥ ቦታ በእሳት ጋይቷል። አውራ ጎዳናዎችንና ሆስፒታሎችን ጨምሮ ወሳኝ የመሠረተ ልማት አገልግሎቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው ሪፖርት ተደርጓል። እሳቱ ቢያንስ የ6,000 ሰዎችን ሕይወት አመሰቃቅሏል፤ ከ1,500 የሚበልጡ ቤቶችም ወድመዋል። እስካሁን ድረስ 25 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • በቶሜ ከተማ እሳት የበላው የአንዲት እህት ቤት፣ ቢዮቢዮ ግዛት

    ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ የለም

  • 222 አስፋፊዎች መኖሪያቸውን ጥለው ለመሸሽ ተገድደዋል፤ 76ቱ አሁንም ወደ ቤታቸው መመለስ አልቻሉም

  • 18 መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል

  • በስብሰባ አዳራሾች ላይ ጉዳት አልደረሰም

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • በአካባቢው ያሉት የጉባኤ ሽማግሌዎችና የወረዳ የበላይ ተመልካቾች በአደጋው ለተጎዱት መንፈሳዊ እርዳታ እያደረጉ ነው

  • የእርዳታ ሥራውን ለማደራጀት የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል

“በሚደርስብን መከራ ሁሉ [የሚያጽናናን]” አምላካችን ይሖዋ ነው፤ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንም ይህን በመተማመን እሱ ከጎናቸው እንደሚሆን እርግጠኞች መሆን ይችላሉ።—2 ቆሮንቶስ 1:4