ኅዳር 13, 2020
ናይጄርያ
በናይጄርያ የተከሰተው አውዳሚ ጎርፍ
መስከረምና ጥቅምት 2020 ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ በናይጄርያ የተለያዩ ግዛቶች ላይ ጎርፍ አስከትሏል። ጎርፉ በእርሻና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። የሚያሳዝነው፣ አንድ ወንድማችን በዚህ ምክንያት ሕይወቱን አጥቷል። በተጨማሪም ከ1,828 የሚበልጡ አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን ቢያንስ 62 የሚያህሉ የወንድሞች ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የናይጄርያ ቅርንጫፍ ቢሮ ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙ የደህንነት ደንቦችን ባገናዘበ መልኩ የእርዳታ ሥራውን እንዲያስተባብሩ ሰባት የአደጋ ጊዜ እርዳታ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል። የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው ያሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች በአደጋው ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በቁሳዊም ሆነ በመንፈሳዊ ለመርዳት ጥረት እያደረጉ ነው።
በዚህ አደጋ ምክንያት አንዳንዶች ሕይወታቸውን እንዳጡ በመስማታችን በጣም አዝነናል። የሚያድነን አምላካችን ይሖዋ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ወንድሞቻችንን ማጽናናቱንና መደገፉን እንደሚቀጥል እንተማመናለን።—መዝሙር 68:19