በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በሪቨርስ ስቴት የሚገኝ በጎርፍ የተጥለቀለቀ ቤት

ጥቅምት 21, 2022
ናይጄርያ

“እጅግ አስከፊ” የተባለለት የናይጄርያ የጎርፍ አደጋ

“እጅግ አስከፊ” የተባለለት የናይጄርያ የጎርፍ አደጋ

በናይጄርያ የተከሰተውን ያልተለመደ ኃይለኛ ዝናብ ተከትሎ በአሥርተ ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የጎርፍ አደጋ ደርሷል። በዚህ አደጋ ክፉኛ የተጎዱት በደቡባዊ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ እንዲሁም በኒጀር እና በቤኑ ወንዞች ዳርቻ ያሉ አካባቢዎች ናቸው። ጎርፉ መሠረተ ልማት አውድሟል፤ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን አፈናቅሏል፤ ቢያንስ 600 ሰዎችም በአደጋው ሞተዋል። የናይጄርያ ብሔራዊ የአደጋ ቁጥጥር ኤጀንሲ ይህን የጎርፍ አደጋ “እጅግ አስከፊ” ሲል ገልጾታል። አደጋው ያደረሰው መጠነ ሰፊ ውድመት የምግብ ቀውስ እንዳያስከትል ባለሥልጣናት ሰግተዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

    አንድ ወንድም በጎርፍ የተጥለቀለቀን አካባቢ ለቆ ሲወጣ

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ የለም

  • 4,074 አስፋፊዎች ተፈናቅለዋል

  • በአሁኑ ወቅት 900 መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል

  • 180 መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል

  • 70 የስብሰባ አዳራሾችና 1 የትላልቅ ስብሰባዎች አዳራሽ በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • 4 የእርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል

  • የተፈናቀሉ አስፋፊዎች ምግብ፣ ጊዜያዊ መጠለያና ሌሎች መሠረታዊ ነገሮች እየተሟሉላቸው ነው

  • የየጉባኤው ሽማግሌዎችና የወረዳ የበላይ ተመልካቾች በአደጋው ለተጎዱ አስፋፊዎች እረኝነት እያደረጉና ተግባራዊ ድጋፍ እየሰጡ ነው

  • የእርዳታ እንቅስቃሴው የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

የምንኖረው አስቸጋሪ በሆነ ዘመን ውስጥ ቢሆንም ይሖዋ በአካላዊም ሆነ በመንፈሳዊ ‘በመዓት ቀን ሕዝቡን በመጠለያው እንደሚሸሽግ’ በማወቃችን አመስጋኞች ነን።—መዝሙር 27:5