በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ታኅሣሥ 27, 2019
ናይጄርያ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በቲቭ ቋንቋ ወጣ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በቲቭ ቋንቋ ወጣ

የናይጄርያ ቅርንጫፍ ቢሮ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ዊልፍሬድ ሲመንስ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በቲቭ ቋንቋ መውጣቱን ታኅሣሥ 20, 2019 አበስሯል። መጽሐፍ ቅዱሱ መውጣቱ የተገለጸው በናይጄርያ፣ ቤንዌይ ክልል ውስጥ በማኩርዲ ሲቲ ቤይ ኢቬንት ሴንተር በተካሄደው “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! በተባለው የክልል ስብሰባ ላይ ነበር።

ለመተርጎም ሁለት ዓመት ገደማ የወሰደው ይህ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ጊዜ መውጣቱ ወቅታዊ ነው። ቲቭ በናይጄርያ ውስጥ በስፋት ከሚነገሩ ቋንቋዎች አንዱ ሲሆን ከአምስት ሚሊዮን በላይ ተናጋሪዎች አሉት። የቲቭ ቋንቋ በሚነገርበት ክልል ውስጥ ያለው የአስፋፊዎች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ከ600 አንስቶ 1,012 ደርሷል።

ይህ አዲስ መጽሐፍ ቅዱስ ‘አዝመራው በነጣበት’ የቲቭ ቋንቋ ክልል ውስጥ ለሚኖረው እድገት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው እንተማመናለን።—ዮሐንስ 4:35