በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ታኅሣሥ 11, 2019
አልባኒያ

የተሻሻለው አዲስ ዓለም ትርጉም በአልባኒያኛ ወጣ

የተሻሻለው አዲስ ዓለም ትርጉም በአልባኒያኛ ወጣ

ታኅሣሥ 8, 2019 ቲራና፣ አልባኒያ ውስጥ በሚገኘው በአስላን ሩሲ ስፖርትስ ፓላስ ውስጥ በተደረገው ልዩ ስብሰባ ላይ የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ማርክ ሳንደርሰን አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በአልባኒያኛ መውጣቱ አበሰረ። a

አልባኒያ ውስጥ 2.9 ሚሊዮን ሰዎች እንደሚኖሩ ይገመታል። ይሁንና በዓለም ዙሪያ የአልባኒያኛ ቋንቋን የሚናገሩ 7.6 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ሰዎች አሉ። የይሖዋ ምሥክሮች በሰሜን መቄዶንያ፣ በስዊዘርላንድ፣ በስዊድን፣ በቤልጅየም፣ በቱርክ፣ በእንግሊዝ፣ በኦስትሪያ፣ በካናዳ፣ በዩናይትድ ስቴትስ፣ በጀርመን፣ በግሪክ፣ በጣሊያንና በፈረንሳይ ውስጥ በአልባኒያኛ ቋንቋ ጉባኤዎችንና ቡድኖችን አቋቁመዋል። ተሻሽሎ የወጣው መጽሐፍ ቅዱስ በአልባኒያ ቅርንጫፍ ቢሮ ክልል ሥር ላሉት ከ5,800 የሚበልጡ አስፋፊዎች እንዲሁም ለአልባኒያ ዲያስፖራዎች ጥቅም እንደሚያስገኝ ተስፋ እናደርጋለን።

የተሻሻለው መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ተጨማሪ መረጃ፣ የግርጌ ማስታወሻ፣ የቃላት መፍቻና ካርታዎች ያሉ ተጨማሪ ገጽታዎችን ያካተተ ነው። የአልባኒያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በጽሑፍ የሰፈረውን የይሖዋን ቃል ቀላል፣ ቀጥተኛና ግልጽ በሆነ ቋንቋ በማግኘታቸው በጣም ተደስተናል።—ማቴዎስ 13:16

a ሙሉው አዲስ ዓለም ትርጉም በአልባኒያኛ የወጣው በ2005 ነበር።