በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 15, 2023
አርጀንቲና

በአርጀንቲና የባሕል ፌስቲቫል ላይ የተካሄደ የአደባባይ ምሥክርነት

በአርጀንቲና የባሕል ፌስቲቫል ላይ የተካሄደ የአደባባይ ምሥክርነት

ከኅዳር 11 እስከ 21, 2022 በሮሳሪዮ፣ አርጀንቲና 38ኛው ዓመታዊው ብሔራዊ የስደተኛ ማኅበረሰቦች ፌስቲቫል ተካሂዷል። ከአንድ ሚሊዮን በላይ ጎብኚዎች ፕሮግራሙን ታድመዋል፤ በአገሪቱ ያሉ የተለያዩ ብሔረሰቦችና ጎሳዎች ባሕልና ልማድ ለእይታ ቀርበዋል። የአርጀንቲና ቅርንጫፍ ቢሮ jw.org ድረ ገጻችንን የሚያስተዋውቅ ልዩ የምሥክርነት ዘመቻ አካሂዷል፤ ለጎብኚዎቹም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች ተበርክተዋል። ሄይቲኛ ክሪኦል፣ ስፓንኛ፣ ቻይንኛ፣ አርጀንቲና ምልክት ቋንቋ፣ እንግሊዝኛ፣ ኬችዋ (ቦሊቪያ)፣ ግዋራኒ፣ ፖርቱጋልኛ ጽሑፎቹ የቀረቡባቸው ቋንቋዎች ናቸው። ከ400 በላይ ወንድሞችና እህቶች በምሥክርነት ዘመቻው ተሳትፈዋል።

የፌስቲቫሉ አዘጋጆች፣ ወንድሞቻችን በተለያዩ ጉልህ ቦታዎች ላይ የጽሑፍ ጋሪ እንዲያቆሙ ፈቀዱላቸው። አንድ የከተማዋ ባለሥልጣን እንዲህ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፦ “ሁላችሁም አለባበሳችሁ ሥርዓታማ ነው፤ ምግባራችሁም ምሳሌ የሚሆን ነው።” በሮሳሪዮ የሚኖር አንድ የሥነ ልቦና ባለሙያ ወደ ጽሑፍ ጋሪው ቀረብ ብሎ ወንድሞችን እንዲህ አላቸው፦ “ጽሑፎቻችሁን በደንብ ነው የማውቃቸው፤ በጣም ደስ ይሉኛል! ብዙውን ጊዜ ታካሚዎቼን ለመርዳት እጠቀምባቸዋለሁ።”

ኅዳር 14, 2022 ላ ካፒታ የተባለው የሮሳሪዮ ከተማ ታዋቂ ጋዜጣ ስለ ስብከት ዘመቻው አንድ ዘገባ አውጥቶ ነበር። ዘገባው የ​jw.org​ን ሊንክ ያካተተ ከመሆኑም ሌላ ድረ ገጻችን ስለሚገኝባቸው ቋንቋዎች ብዛት መረጃ ሰጥቷል።

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ‘ምሥራቹን በተሟላ ሁኔታ ለመመሥከር’ የሚያደርጉት ጥረት ያስደስተናል።—የሐዋርያት ሥራ 20:24