በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

አዲሱ የአርጀንቲና ቤቴል ሲወሰን የቤቴል ቤተሰብ አባላት እንግዶችን ሲቀበሉ

ሚያዝያ 22, 2024
አርጀንቲና

አርጀንቲና ውስጥ አዳዲስ የቅርንጫፍ ቢሮ ሕንፃዎች ተወሰኑ

አርጀንቲና ውስጥ አዳዲስ የቅርንጫፍ ቢሮ ሕንፃዎች ተወሰኑ

ወንድም ጄፍሪ ዊንደር የውሰና ንግግር ሲሰጥ

ሚያዝያ 6, 2024 ቡነስ አይረስ፣ አርጀንቲና ውስጥ አዳዲስ የቅርንጫፍ ቢሮ ሕንፃዎች ተወስነዋል፤ በውሰና ፕሮግራሙ ላይ ንግግር የሰጠው የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ጄፍሪ ዊንደር ነው። በአዲሱ ቤቴል በሚገኙ ሦስት አዳራሾች ውስጥ 500 ገደማ ወንድሞችና እህቶች የውሰና ፕሮግራሙን ታድመዋል። በአቅራቢያው ካለችው የኤዜይዛ ከተማ ደግሞ 5,844 ተሰብሳቢዎች በትላልቅ ስብሰባዎች አዳራሽ ውስጥ ሆነው ፕሮግራሙን በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተከታትለዋል። በቀጣዩ ቀን በትላልቅ ስብሰባዎች አዳራሽ ውስጥ ልዩ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን ፕሮግራሙ በአርጀንቲና እና በኡራጓይ ወዳሉ ጉባኤዎች በሙሉ በቀጥታ ተላልፏል፤ በድምሩ 181,643 ተሰብሳቢዎች ነበሩ።

እንግዶች አዳዲሶቹን ሕንፃዎች የሚጎበኙበት፣ እርስ በርስ ደስ የሚል ጊዜ የሚያሳልፉበትና ለየት ባሉ ሌሎች እንቅስቃሴዎች የሚሳተፉበት ዝግጅት ተደርጓል። ከእንግዶቹ መካከል ከ25 አገራት የመጡ ከ230 በላይ ወንድሞችና እህቶች ይገኙበታል። አሁን ኢኳዶር ውስጥ የሚያገለግለው ወንድም ሰርኺዮ ስፓካሳሲ በአርጀንቲና ቅርንጫፍ ቢሮ ግንባታ ተሳትፏል። በውሰና ፕሮግራሙ ላይ ከተለያዩ አገራት የተገኙትን ታዳሚዎች አስመልክቶ እንዲህ ብሏል፦ “እንዲህ ያሉ ልዩ ስብሰባዎች ይሖዋ እንደ ቤተሰብ አንድነታችንን የሚያጠናክርባቸው ግሩም አጋጣሚዎች ናቸው።”

የአርጀንቲና ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ሁዋን ካርሎስ ኒግሮ እንዲህ ብሏል፦ “ይሖዋ ይህን ፕሮጀክት በእያንዳንዱ ምዕራፍ እንዴት እንደመራውና እንደባረከው ተመልክተናል። ስሙን የሚያስከብረውን ይህን ውብ ሕንፃ የሰጠን እሱ ነው።”

ወንድሞችና እህቶች ቡነስ አይረስ ውስጥ ከሚገኘው አዲሱ የቤቴል አዳራሽ ሆነው የውሰና ፕሮግራሙን ሲከታተሉ

“ሁሉንም ነገር በወቅቱ ውብ አድርጎ” የሚሠራውን ይሖዋን ከአርጀንቲና ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር ለዚህ አዲስ የቤቴል ሕንፃ እናመሰግነዋለን።​—መክብብ 3:11