በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 2, 2022
አርጀንቲና

የአርጀንቲና ቤቴል ቤተሰብ አባላት ወደ አዲሱ ቤታቸው ገቡ

የአርጀንቲና ቤቴል ቤተሰብ አባላት ወደ አዲሱ ቤታቸው ገቡ

የአርጀንቲና ቤቴል ቤተሰብ አዲስ ወደተገነባው የቅርንጫፍ ቢሮ የሚያደርገውን ዝውውር አጠናቅቋል። ግንባታውን ያከናወነው ከድርጅቱ ውጭ ያለ ተቋራጭ ሲሆን ሥራው በ2021 የክረምት ወቅት ተጠናቋል። ከዚያ ጊዜ ወዲህ ቤቴላውያንና የግንባታ ፈቃደኛ ሠራተኞች የአዲሱን ሕንፃ የማጠናቀቂያ ሥራዎች ሲያከናውኑ ቆይተዋል፤ ይህም የቤት ዕቃዎችን መገጣጠምን፣ ጽዳትን፣ የቧንቧ ሥራንና የኤሌክትሪክ ሥራን ያካትታል።

አዲሱ ቤቴል 136 የሥራ ቦታዎችን የያዘ የቢሮ ሕንፃና 98 ክፍሎች ያሏቸው ሁለት የመኖሪያ ሕንፃዎችን ያካትታል። የቀድሞው ቅርንጫፍ ቢሮ የሚጠቀመው በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ሕንፃዎችን ነበር። አዲሱ ቅርንጫፍ ቢሮ ቤቴላውያን በአንድ ቦታ እንዲሠሩና እንዲኖሩ ያስችላል። መሬቱ በአጠቃላይ 8,524 ካሬ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን የሚገኘው የአርጀንቲና ዋና ከተማ ከሆነችው ከቦነስ አይረስ ወጣ ብሎ ነው።

የቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ሁምቤርቶ ካይሮ እንዲህ ብሏል፦ “ይሖዋ ከዚህ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ታላቅ ልግስና አሳይቶናል። አዲሶቹ ሕንፃዎች በጣም ውብ ናቸው፤ በሕንፃው ላይ ያለው የ​jw.org ምልክትም በቀላሉ ይታያል።”

በአገልግሎት ዘርፍ የሚያገለግለው ወንድም ሴባስቲያን ሮሶ እንዲህ ብሏል፦ “ይሖዋ ግሩም ስጦታ ሰጥቶናል። ልክ ለእኛ እንዲመች ታስቦ የተዘጋጀ ቦታ ነው። እንዲህ ያለ ማራኪና ለሥራ አመቺ ቅርንጫፍ ቢሮ በማግኘታችን በጣም አመስጋኞች ነን።”

ይህ አዲስ ቅርንጫፍ ቢሮ የቤቴል ቤተሰብ ሥራውን ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲያከናውን እንደሚያስችለው እንተማመናለን። በተጨማሪም ለማኅበረሰቡ ግሩም ምሥክርነት እንደሚሰጥና ለይሖዋ ክብር እንደሚያመጣ እርግጠኞች ነን።—2 ዜና መዋዕል 7:1

 

የአርጀንቲና የቤቴል ቤተሰብ በቦነስ አይረስ ወደሚገኘው አዲስ ቅርንጫፍ ቢሮ ተዛውሯል። ቤተሰቡ ወደ አዲሱ ቅርንጫፍ ቢሮ መዛወር የጀመረው ሐምሌ 2021 ነው፤ እንቅስቃሴው የተደረገው ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ተከትሎ ነው። ቤቴላውያኑ ከተዛወሩ በኋላ የቤት ዕቃዎችን መገጣጠምንና ጽዳትን ጨምሮ አንዳንድ የማጠናቀቂያ ሥራዎችን አከናውነዋል። አዲሱ ቅርንጫፍ ቢሮ ለማኅበረሰቡ ግሩም ምሥክርነት ይሰጣል