በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥቅምት 14, 2019
አርጀንቲና

የአርጀንቲና ቤቴል ግንባታ ፕሮጀክት ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ

የአርጀንቲና ቤቴል ግንባታ ፕሮጀክት ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ

አዲስ እየተገነባ ያለው የአርጀንቲና ቅርንጫፍ ቢሮ ፀሐይ ስትጠልቅ የተነሳው ፎቶ

የአርጀንቲና ቅርንጫፍ ቢሮ ፕሮጀክት ከተጀመረ አንድ ዓመት ያለፈው ሲሆን 50 በመቶ የሚሆነው ሥራ ተጠናቋል። አዲሱ ቤቴል በድምሩ 8,524 ካሬ ሜትር ላይ ያረፉ ሦስት ሕንፃዎች አሉት፤ አንደኛው ሕንፃ ለቢሮ፣ ሁለቱ ደግሞ ለመኖሪያነት የሚያገለግሉ ናቸው። ግንባታው ሐምሌ 2020 ይጠናቀቃል ተብሎ ይገመታል።

የአርጀንቲና ቅርንጫፍ ቢሮ ግንባታ ያለበት ደረጃ አስደሳች ነው። በዚህ ፕሮጀክት ላይ የይሖዋ እርዳታ እንዳይለየን እንጸልያለን።—ዘዳግም 28:8

 

ሚያዝያ 2019፦ ለቢሮ አገልግሎት የሚውለው ሕንፃ። በሕንፃው መሠረት ላይ የሚታዩት ምሰሶዎች እስከ ሕንፃው መጨረሻ ድረስ የሚወጡ ሲሆን ይህም ሕንፃው ጠንካራ እንዲሆን ይረዱታል

ሰኔ 2019፦ አንድ የግንባታ ሠራተኛ በብረት መወጣጫ ላይ ቆሞ የመኖሪያ ሕንፃ A​ን ምሰሶ ሲሠራ

ሐምሌ 2019፦ የግንባታ ሠራተኞች ለቢሮ አገልግሎት በሚውለው ሕንፃ ሦስተኛ ፎቅ ላይ ለአርማታ የሚሆን ፌሮ እና የኤሌክትሪክ መስመሮችን ሲዘረጉ

ሐምሌ 2019፦ የግንባታ ሠራተኞቹ የመኖሪያ ሕንፃ A​ን ሁለተኛ ፎቅ አርማታ ሲሞሉ። ሕንፃው ባለአራት ፎቅ ሲሆን ሰገነትም ይኖረዋል

ሐምሌ 2019፦ የመኪና ማቆሚያው ሲገነባ። ቦታው ምድር ቤት ውስጥ 72፣ ከላይ ደግሞ ተጨማሪ 72 መኪናዎችን ማቆም ያስችላል

ነሐሴ 2019፦ በስተ ግራ የመኖሪያ ሕንፃ A ይታያል፤ ከመቆፈሪያው በስተ ጀርባ ደግሞ የመኖሪያ ሕንፃ B እና ለቢሮ የሚያገለግለው ሕንፃ ይታያሉ