በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በአርጀንቲና ምልክት ቋንቋ ሲወጣ ተሰብሳቢዎቹ እጃቸውን በማውለብለብ አድናቆታቸውን ሲገልጹ

ጥር 1, 2020
አርጀንቲና

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በአርጀንቲና ምልክት ቋንቋ ወጣ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በአርጀንቲና ምልክት ቋንቋ ወጣ

ታኅሣሥ 13, 2019 በቦነስ አይረስ፣ አርጀንቲና በተካሄደው ብሔራት አቀፍ ስብሰባ ላይ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በአርጀንቲና ምልክት ቋንቋ መውጣቱ ተገለጸ። የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ወደ አርጀንቲና ምልክት ቋንቋ ሲተረጎም ይህ የመጀመሪያው ነው።

የትርጉም ቡድኑ ረጅም ጊዜ የወሰደውን ፕሮጀክት በማቴዎስ መጽሐፍ የጀመረው ታኅሣሥ 3, 2014 ነበር። በምልክት ቋንቋ የተዘጋጁ የሕትመት ውጤቶች የሚቀርቡት በቪዲዮ ስለሆነ የእያንዳንዱ መጽሐፍ የትርጉም ሥራ እንደተጠናቀቀ JW ላይብረሪ ምልክት ቋንቋ የተባለው አፕሊኬሽን ላይ እንዲወጣ ይደረግ ነበር።

አንዳንድ ምንጮች እንደሚገልጹት የአርጀንቲና ምልክት ቋንቋን የሚጠቀሙ 400,000 ገደማ ሰዎች አርጀንቲና ውስጥ አሉ። በተጨማሪም የአርጀንቲና ምልክት ቋንቋን የሚጠቀሙ 2,700 አስፋፊዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 470 የሚሆኑት መስማት የተሳናቸው ናቸው። ሎራ ሎሳንዳ የተባለች በአርጀንቲና ምልክት ቋንቋ የምትጠቀም መስማት የተሳናት አንዲት እህት እንዲህ ብላለች፦ “ይሖዋ ይህን የመሰለ ልግስና ስላሳየን በጣም አመስጋኝና ደስተኛ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ በአርጀንቲና ምልክት ቋንቋ ከመዘጋጀቱ በፊት በስፓንኛ የተዘጋጀውን መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ ከፍተኛ ጥረት አደርግ ነበር፤ ሆኖም የማነበው ነገር አይገባኝም ነበር። አሁን ግን ይህን ግልጽ የሆነ አዲስ ትርጉም ስላገኘሁ ከይሖዋ ጋር ያለኝ ዝምድና እንደተጠናከረ ይሰማኛል።”

የአርጀንቲና ምልክት ቋንቋን የሚጠቀሙ ወንድሞችና እህቶች መንፈሳዊነታቸውን ለማጠናከር የሚረዳቸውን ይህን ለመረዳት ቀላል የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በማግኘታቸው በጣም አመስጋኞች ናቸው። ይህ አዲስ ትርጉም አስፋፊዎች በአርጀንቲና የሚኖሩ መስማት የተሳናቸው ሰዎች የይሖዋ ወዳጅ እንዲሆኑ ለመርዳት በሚያደርጉት ጥረት እንደሚያግዛቸው እንተማመናለን።—የሐዋርያት ሥራ 13:48