በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥር 20, 2021
አንጎላ

አዲስ ዓለም ትርጉም በኡምቡንዱ ቋንቋ ወጣ

አዲስ ዓለም ትርጉም በኡምቡንዱ ቋንቋ ወጣ

ጥር 16, 2021 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በኡምቡንዱ ቋንቋ በኤሌክትሮኒክ ፎርማት ወጣ። ፕሮግራሙ አስቀድሞ የተቀዳ ሲሆን በአንጎላ ለሚገኙ የኡምቡንዱ ቋንቋ ጉባኤዎች በሙሉ ተላልፏል። መጽሐፍ ቅዱሱ መውጣቱን ያበሰረው የአንጎላ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ዤኔዚዮ ቨርዲያኖ ነው።

አንጎላ ውስጥ በስፋት የሚነገረው አገር በቀል ቋንቋ ኡምቡንዱ ነው፤ ሰባት ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ይህን ቋንቋ ይናገራሉ። የኡምቡንዱ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ከ6,500 የሚበልጡ አስፋፊዎች አሉ።

ስድስት ተርጓሚዎችን ያቀፉ ሁለት ቡድኖች ለአምስት ዓመት ያህል በዚህ የትርጉም ሥራ ተካፍለዋል። አንድ ተርጓሚ እንዲህ ብሏል፦ “ይህ አዲስ ትርጉም ለመረዳት ቀላል ስለሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ሕያው እንዲሆኑልን ያደርጋል። በተጨማሪም በአገልግሎት ላይ የአምላክን ቃል ለሌሎች ማስተማር ቀላል እንዲሆንልን ያደርጋል።”

አንድ የቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል እንዲህ ብሏል፦ “ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በራሳቸው ቋንቋ ሲያነቡ እውነት በቀላሉ ይገባቸዋል። ይሖዋ በኡምቡንዱ ቋንቋ የተተረጎመውን ቃሉን ተጠቅሞ ተጨማሪ ሰዎችን የሚረዳው እንዴት እንደሆነ ለማየት ጓጉተናል።”—2 ተሰሎንቄ 3:1