በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ኅዳር 29, 2019
አውስትራሊያ

ሜልበርን፣ አውስትራሊያ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ

ሜልበርን፣ አውስትራሊያ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
  • ቀን፦ ከኅዳር 22-24, 2019

  • ቦታ፦ በሜልበርን፣ አውስትራሊያ የሚገኘው ማርቭል ስታዲየም

  • ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ስፓንኛ፣ ታጋሎግ፣ ቻይንኛ ማንዳሪን፣ ቻይንኛ ካንቶንኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ኮሪያኛ፣ የአውስትራሊያ ምልክት ቋንቋ፣ ቬትናምኛ

  • ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 46,582

  • አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 407

  • ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 6,083

  • የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ሆንግ ኮንግ፣ ሕንድ፣ ሰለሞን ደሴቶች፣ ታይዋን፣ አርጀንቲና፣ ካናዳ፣ ኮሪያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጃፓን፣ ጣሊያን፣ ፊሊፒንስ

  • ተሞክሮ፦ የባላራት የዱር እንስሳት ፓርክ ኃላፊ እንዲህ ብለዋል፦ “በባላራት የዱር እንስሳት ፓርክ በሠራሁባቸው 15 ዓመታት ውስጥ የእናንተን ያህል የተደራጀና ደስ የሚል ቡድን አጋጥሞኝ አያውቅም ብል ማጋነን አይሆንም። ለእናንተም ሆነ ለአስጎብኚዎቻችሁ ከፍተኛ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ።”

    የአንድ ሆቴል ኃላፊም በሆቴላቸው ውስጥ ያረፉትን 340 ልዑካን አስመልክተው ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፦ “ሁሉም ሰው ተባብሮ ችግሮችን ለመፍታት ይጥራል። ልክ እንደ ትልቅ ቤተሰብ እርስ በርስ ትነጋገራላችሁ እንዲሁም ትረዳዳላችሁ። ከሁላችሁም ጋር በመገናኘቴ ደስ ብሎኛል። ሆቴል ውስጥ ስሠራ 11 ዓመት ሆኖኛል፤ ሆኖም እንዲህ ዓይነት ቡድን ገጥሞኝ አያውቅም።” እኚህ ኃላፊ የይሖዋ ምሥክሮች ባሳዩት ምግባር በመደሰታቸው በቅዳሜው ስብሰባ ላይ ለመገኘት ፈቃደኛ ሆነዋል።

 

በአውስትራሊያ ከሲድኒ ከተማ ወጣ ብሎ በዴንሃም ኮርት በሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ ወንድሞችና እህቶች ልዑካኑን ሲቀበሉ

ወንድሞችና እህቶች ወደ ስታዲየሙ ሲገቡ

ልዑካኑ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ሲዘምሩ

አንዲት ወጣት እህት ከተጠመቀች በኋላ እናቷን ስታቅፍ

የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ዴቪድ ስፕሌን የዓርብ ዕለቱን የመደምደሚያ ንግግር ሲያቀርብ

ልዑካን ሆነው የመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ለተሰብሳቢዎቹ ሰላምታ ሲሰጡ

ልዑካኑ አብረው ፎቶ ሲነሱ

እህቶች ምሽት ላይ በተዘጋጀው የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ ውዝዋዜ ሲያቀርቡ